በደቡብ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ስቃይ እንደደረሰባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ

በደቡብ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ስቃይ እንደደረሰባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) በእስር ቤት ውስጥ ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ናቸው። በርካታ ሴቶችም በእስር ቤት ውስጥ ተደፍረዋል።
የደቡብ ሱዳን መንግስት የሚቀርብበትን ትችት እንደማይቀበል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል።
የፕሬዚዳንት ሳለቫኪር ቃል አቀባይ አቴንግ ዋግ አቴንግ የአምነስቲን ሪፖርት አስተባብለው በቅርቡ 20 የፖለቲካ እስረኞች መፈታታቸውን ገልጸዋል።