በሊቢያ ከ400 በላይ እስረኞች አመለጡ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 28/2010) በሊቢያ ትሪፖሊ በእስር ቤት የነበሩ ከ400 በላይ እስረኞች ከእስር ቤት ማምለጣቸው ተሰማ።

ለእስረኞቹ ያመለጡት በከተማዋ  ትሪፖሊ በተቃዋሚ አንጃዋች መካከል ከፍተኛ የተኩስ  ልውውጥ መከሰቱን ተከትሎ ነው ብሏል ቢቢሲ በዘገባው።

የእስር ቤት ጠባቂዎቹ ለደህንነትቸው በመስጋት ሲሸሱ እስረኞች ደግሞ የእስር ቤቱን በር በመስበር ለመውጣት መገደዳቸው ታውቋል።

አኒ ዛራ በተባለው እስር ቤት ውስጥ ከነበሩት አብዛኛዎቹ የቀድሞው የሊቢያ ፕሬዘዳንት ደጋፊ የነበሩና በ2011 በሀገሪቱ በነበረው ረብሻ የሰው ሕይወት አጥፍተዋል  በሚል የታሰሩ እንደነበሩ ዘገባው አስታውሷል።

ሊቢያ ፕሬዝዳንት ሙሀመድ ጋዳፊ  ከስልጣን ከተወገዱበት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2011 ወዲህ ሰላም እንደራቃት ነው።