ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ሰመራ ገቡ

ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ሰመራ ገቡ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሱልጣኔ በአፋር ዋና ከተማ ሰመራ ሲደርሱ ህዝቡ ወጥቶ ደማቅ አቀባባል አድርጎላቸዋል። በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአፋር ክልል መሪ የነበሩት ሱልጣን ሃንፍሬ፣ ከህወሃት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከስልጣናቸው እንዲወርዱ በመደረጉ ለስደት ተዳርገዋል።
በኢትዮጵያ የሚታየውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ አገራቸው የተመለሱት ሱልጣኑ፣ በክልሉ በሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዋና ተዋናይ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአፋር ህዝብ ላይ 27 አመታት የደረሰውን የመብት ረገጣ ተከትሎ በርካታ አፋሮች አገራቸውን ለቀው መሰደዳቸው ይታወቃል።