ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአሰብ እና ምጽዋ ወደቦችን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአሰብ እና ምጽዋ ወደቦችን ጎበኙ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሃያ ዓመታት በላይ ግንኙነታቸውን አቋርጠው የነበሩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቀ ሰላም በማድረግ ከመሪዎች እና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነነት በተጨማሪ የወደብና የንግድ ሥራዎች በይፋ ጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአሰብ ወደብ አየር ማረፊያ በማቅናት ወደቡንና ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውን የጥርጊያ መንገድ ጎብኝተዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው የመንገዱ እና የወደቡ ይዞታ በጥሩ ሁኔታ ላይ ንደሚገጭ በመግለጽ፤ የተሻለ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የማስተካከያ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ አገልግሎት መስጠት ይጀምራልም ብለዋል።
ከአሰብ በመቀጠል በምጽዋ ወደብ በመገኘት ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሁለቱም መሪዎች በቀጣይ የምስራቅ አፍሪካ በየነ መንግስታት ኢጋድ ጉዳይን አስመልክቶ የጋራ ውውይት ማድረጋቸውም ታውቋል።
ንብረትነቷ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት የሆነችው መቀሌ በመባል የምትታወቀው መርከብ በምጽዋ ወደብ መኅልቋን በመጣል የጭነት እቃዎችን ወደ ቻይና ይዛ እንደምትጓዝ ታውቋል። ይህ የሁለቱ አገራት የሰላም እና የኤኬኖሚ ትስስር ለቀጠናው ሰላም መስፈን ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ተብሎለታል። በተለይም ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከተሾሙ ወዲህ በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ የታየው አንጻራዊ ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱን የፖለቲካ ተንታኞች ይገልጻሉ።