(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 5/2010)በኢትዮጵያ ነጻነት እንዲመጣ መስዋዕትነት የከፈሉ ኢትዮጵያውያኖች በተለይም ቄሮዎች ፋኖዎች ሊወደሱ እንደሚገባ አክቲቪስት ታማኝ በየነ ገለጸ። አክቲቪስት ታማኝ በየነ ይህን መልዕክት ያስተላለፈው በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚያደርገውን ጉብኝት በመቀጠል በሳምንቱ መጨረሻ ከአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ባደረገው ቆይታ ነው። አክቲቪስት ታማኝ በየነ ሕዝባዊውን ትግል አስተባብረው የጨለማው ዘመን እንዲያበቃ ፊት ለፊት ለተጋፈጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና በአጠቃላይ ለለውጡ ቡድን ያለውን ክብር ገልጿል። ...
Read More »የጸጥታ ሃይሎች የጸጥታ ስጋት እየሆኑ መምጣታቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 5/2010)በየክልሉ ያሉ የጸጥታ ሃይሎች ከጸጥታ ማስከበር ይልቅ የጸጥታ ስጋት እየሆኑ መምጣታቸው ተገለጸ። አንዳንድ ክልሎች በድንበር አካባቢ ታጣቂዎችን እያሰባሰቡ መሆናቸውንም የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን ገልጸዋል። በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ የሆኑት ሜጀር ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና ይህንን የተናገሩት መቀሌ በተካሄደ የመከላከያ ሰራዊት ስብሰባ ላይ ነው። የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመና ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል ሰአረ መኮንን በተገኙበት ትላንት ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለሐገሪቱ መረጋጋትና የተቋማት ግንባታ ትኩረት እሰጣለሁ አለ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 5/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ዲሞክራሲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ለሐገሪቱ መረጋጋትና የተቋማት ግንባታ እንጂ ለምርጫ አይደለም ሲሉ ተናገሩ። የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የገለጹት ከ10 አመታት ስደትና ትግል በኋላ ትላንት ወደ ሃገራቸው በገቡበት ወቅት ነው። በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ደማቅ የአቀባበል ስነስርአት ላይ ከዋና ጸሐፊው አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ከሌሎች የአመራሩ ...
Read More »የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎችን ተቀበለ
የአዲስ አበባ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎችን ተቀበለ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 05 ቀን 2010 ዓ/ም ) የከተማው ህዝብ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌንና ጨምሮ ሌሎችንም የንቅናቄው አመራሮችና አባላትን ለመቀበል ከጠዋት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ሰታዲየም በመሄድ እንግዶችን እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎአል። ህዝቡ ኮከብ የሌለበትን ሰንደቃላማ በመያዝ በጭፈራ፣ በዝማሬና የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ደስታውን ሲገልጽ ውሎአል። ዝግጀቱን በተመለከተ ...
Read More »የአዴሃን ሃይሎች ወደ አገራቸው ገቡ
የአዴሃን ሃይሎች ወደ አገራቸው ገቡ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 05 ቀን 2010 ዓ/ም ) የህወሃትን አገዛዝ በመቃወም የትጥቅ ትግል ሲያካሂዱ የቆዩ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ አመራሮችና የሰራዊ አባላት ወደ አገራቸው ገብተዋል። የሰራዊቱ አባላት ወደ አገር ሲገቡ የጎንደርና የሌሎችም ከተሞች ነዋሪዎች በመንገዱ ላይ በመውጣት የጀግና አቀባበል አድርገውላቸዋል። አዴሃን ከመንግስት ጋር ከተነጋገረ በሁዋላ ወደ አገር ቤት የገባ ሲሆን፣ የድርጅቱ አመራሮች በሰላማዊ መንገድ ...
Read More »ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ማቋረጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
ከደቡብ ሱዳን የመጡ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ማቋረጣቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 05 ቀን 2010 ዓ/ም ) በርካታ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደ ጋምቤላ መግባታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ በአኝዋኮች ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ ስለሚችሉ የመከላከያ አባላት እንዲያውቁት ይደረግ በማለት ጠይቀዋል። ታጣቂዎች የማን ሃይል እንደሆኑ ነዋሪዎች ለመግለጽ አልቻሉም። ከዚህ በፊት ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ ታጣቂዎች ወደ ጋምቤላ ክልል በመግባት በርካታ ዜጎችን እያፈኑ ...
Read More »ኤርትራና ጅቡቲ ስምምነት ላይ ደረሱ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 2/2010) ኤርትራና ጅቡቲ በመካከላቸው የነበረውን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ። ሁለቱም ሃገራት ዱሜራ በተባለ ተራራና ደሴት ይገባኛል ጥያቄ ላለፉት 12 አመታት ሲወዛገቡ መቆየታቸው ይታወሳል። በኢትዮጵያ ሸምጋይነት የተጀመረው ጥረት ተሳክቶ ኤርትራና ጅቡቲ ችግሮቻቸውን በሰላም ለመፍታት ተስማምተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳስታወቁት በኤርትራና ጅቡቲ መካከል የነበረውን አለመግባባት በሰላም ለመፍታት መወሰኑ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ...
Read More »የፖሊስ የምርመራ ስራ ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው ነበር ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 2/2010) በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የሚካሄደው የፖሊስ የምርመራ ስራ ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ገለጹ። በአሁኑ ወቅት ስራዎች የሚሰሩት ሙያውንና ሕግን መሰረት በማድረግ ብቻ ነው ሲሉም ተናግረዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ይህን የተናገሩት የኢንጅነር ስመኘውን ሕልፈት በተመለከተ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው። ከኢንጅነር ስመኘው ግድያ ጋር በተያያዘ በተጠራው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ...
Read More »ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ነው ያጠፉት ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 2/2010) ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን በምርመራ ማረጋገጡ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽነሩ ከሌሎች ሃላፊዎች ጋር በመሆን በሰጡት መግለጫ ኢንጂነሩ ራሳቸውን ስለማጥፋታቸው መረጃዎች መገኘታቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻ ሰአት ያደረጓቸው የስልክ ልውውጦችም ሆኑ በመጨረሻ አካባቢ ያሳዩት የነበረው ባህሪ ራሳቸውን ለማጥፋታቸው ማሳያ ናቸው ሲል በሪፖርቱ ላይ ተመልከቷል። የምርመራው ሪፖርቱን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች በመሰንዘር ላይ ናቸው። በተደጋጋሚ ይፋ ይሆናል የተባለው የኢንጅነር ስምኘው ...
Read More »የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስና መሪ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፖሊስ አስታወቀ
የአባይ ግድብ ዋና መሃንዲስና መሪ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ራሳቸውን ማጥፋታቸውን ፖሊስ አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል በመሩት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ፖሊስ ኢንጂነር ስመኛው ራሳቸውን አጥፍተዋል የሚል መደምደሚያ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል። እዚህ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ የተለያዩ ማስረጃዎችንና የጥናት ዘዴዎችን መጠቀማቸውን የገለጹት መርማሪ ፖሊሶቹ፣ ለዚህ ድምዳሜ ያደረሱዋቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች ከመሞታቸው በፊት ...
Read More »