የፖሊስ የምርመራ ስራ ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው ነበር ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 2/2010) በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የሚካሄደው የፖሊስ የምርመራ ስራ ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ገለጹ።

በአሁኑ ወቅት ስራዎች የሚሰሩት ሙያውንና ሕግን መሰረት በማድረግ ብቻ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ይህን የተናገሩት የኢንጅነር ስመኘውን ሕልፈት በተመለከተ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ነው።

ከኢንጅነር ስመኘው ግድያ ጋር በተያያዘ በተጠራው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰኔ 16ቱን የቦምብ ጥቃት ምርመራ ውጤት ለምን ዘገየ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል።

ለዚህም በሰጡት ምላሽ ምርመራው ሙያዊ በሆነ መንገድ እየተሰራ በመሆኑ መዘግየቱን ገልጸዋል።

እንደከዚህ ቀደሙ ሙያዊ ባልሆነ መንገድ አይሰራም ሲሉም ተናግረዋል።

ምርመራው ሙያዊ በሆነ መንገድ ብቻ እንደሚካሄድም ተናግረዋል።