የረጲ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በተመረቀ በሁለት ሳምንቱ ስራ አቆመ

የረጲ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በተመረቀ በሁለት ሳምንቱ ስራ አቆመ ( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ ከተማ 2.6 ቢሊዮን ብር ወጪ ወጥቶበት የተገነባው የረጲ ደረቅ ቆሻሻ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ነሐሴ 13 ቀን 2010 ዓ.ም. ቢመረቅም በሁለት ሳምንቱ ስራውን አቋርጧል። ለፕሮጀክቱ አገልግሎት መቋረጥ ያልተጠናቀቁ ሥራዎች መኖራቸውን በምክንያትነት ቢጠቀስም፣ የካምብሪጅ ኢንዱስትሪስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ዓለማየሁ ግን ...

Read More »

ታዋቂው የነጻነት ታጋይ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ መታመማቸው ታወቀ

ታዋቂው የነጻነት ታጋይ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ መታመማቸው ታወቀ ( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) በኢትዮጵያ የቀድሞው ሰራዊት ውስጥ በአየር ሃይል ምድብ ከፍተኛ ወታደራዊ ጀብዱ በመፈጸም የተለያዩ የጀግና ሜዳሊያዎችን የተሸለሙት የቀድሞው የአርበኞች ግንባር መሪ ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ታመው ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ኮ/ል ታደሰ አስመራ ውስጥ ኦሮታ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝተው ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ በፍጥነት ሄደው ለመታከም ...

Read More »

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ኮፊ አናን የቀብር ስነስርዓት በተውልድ አገራቸው ተፈጸመ

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ኮፊ አናን የቀብር ስነስርዓት በተውልድ አገራቸው ተፈጸመ ( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በዋና ጸሃፊነት የመሩት ጋናዊው ኮፊ አናን የቀብር ስነስርዓት የተለያዩ አገር መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በትውልድ አገራቸው ጋና መዲና አክራ ውስጥ ተፈጸመ። ኮፊ አናን በተለያዩ የስልጣን እርከኖች አገራቸውን፣ አህጉራቸውን ጨምሮ ትልቁን ተቋም ተመድን ከመምራታቸውም በላይ ...

Read More »

በአሜሪካ ምስራቃዊ ክፍል ላይ ያንዣበበው አውሎ ንፋስ ሰዎችን ማፈናቀል ጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 2/2011) በዩናይትስ ስቴትስ አሜሪካ ምስራቃዊ ክፍል ላይ ያንዣበበው ዝናብ የቀላቀለ ከፍተኛ አውሎ ንፋስ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ማፈናቀል ጀመረ። የፌደራል መንግስቱ አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቃል የገቡ ሲሆን ከሩብ ክፍለ ዘመን ወዲህ በአይነቱ አደገኛው አውሎ ንፋስ መሆኑም ተመልክቷል። ፍሎረንስ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ አውሎ ንፋስ በሰአት 130 ማይል እየበረረ እንደሚጓዝ ተገምቷል። በዩናይትድ ስቴትስ  አሜሪካ ምስራቃዊ ...

Read More »

የኢሕአዴግና አባል ድርጅቶች ጉባኤ ሊጀመር ነው

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 2/2011)የኢሕአዴግና አባል ድርጅቶቹ ጉባኤዎች ከአርብ ጀምሮ እንደሚካሄድ ታወቀ። የኢሕአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በነገው ዕለት የሚካሄድ ሲሆን የኦሕዴድ 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት በጅማ ከተማ እንደሚጀመር ተዘግቧል። ብአዴን ሕወሃትና ደኢሕዴንም በተመሳሳይ ጉባኤያቸውን በዚሁ በመስከረም ወር እንደሚያደርጉም ተገልጿል። በመጨረሻም የኢሕአዴግ ጉባኤ በሃዋሳ እንደሚካሄድም ተመልክቷል። የፊታችን አርብ የሚጀመረው የኢሕአዴግ ምክር ቤት በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ በቀረቡ አጀንዳዎች ላይ እንደሚወያይና በመስከረም ...

Read More »

የትሕዴን መሪዎች አዲስ አበባ ገቡ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 2/2011) መቀመጫቸውን ኤርትራ በማድረግ የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ የነበሩት የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ትብብር/ትሕዴን/ መሪዎች አዲስ አበባ ገቡ። በትሕዴን ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬና በዋና ጸሃፊው አቶ ግደይ አሰፋ የተመራው የልኡካን ቡድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ሃይለሚካኤል ተቀብለውታል። ትላንት ማክሰኞ መስከረም 1 ቀን 2011 አዲስ አበባ የገቡት የትህዴን መሪዎች ላለፉት 17 አመታት ያህል የሕወሃት/ኢሕአዴግን መንግስት በመቃወም በትጥቅ ትግል ላይ ...

Read More »

የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 2/2011) የግጭት ነጋዴዎችን ሴራ እናክሽፍ ሲሉ የጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ጥሪ አደረጉ። ሃላፊው አቶ ታዬ ደንደአ በግል የማህበራዊ መድረካ ላይ ባስተላልፉት ጥሪ ኢትዮጵያውያን ከትንንሽ አጀንዳዎች ወጥተው ስለሀገር ከልብ እንዲያስቡ ጠይቀዋል። አቶ ታዬ ይህን መልዕክት ያስተላለፉት ዛሬ በአዲስ አበባ ከሰንደቅ ዓላማና አርማ ጋር በተያያዘ የተፈጠረውን መለስተኛ ግጭት ተከትሎ ነው። የኦሮሞ ነጻነግ ግንባር መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳን ለመቀበል ...

Read More »

ልማት ባንክ ዛሬም ድረስ በህወሃት ቁጥጥር ስር መሆኑን ምንጮች ገለጹ

ልማት ባንክ ዛሬም ድረስ በህወሃት ቁጥጥር ስር መሆኑን ምንጮች ገለጹ ( ኢሳት ዜና መስከረም 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) ባንኩ ለአማራ ባለሃብቶች ሆን ብሎ ብድር እንዳይሰጥ እንደሚያደርግ በባንኩ ውስጥ የሚሰሩ ምንጮች ለኢሳት በላኩት ዝርዝር መረጃ አመለክተዋል። ባንኩን ለመምራት እድል ያገኙት የልማት ባንክ ፕረዝዳንቶች፣ ምክትል ፕረዝዳንቶች እና ዳይሬክተሮች የስልጣን መሰረታቸው የተደራጁ እና በጥቅም የተሳሰሩ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ዘራፊ ባለሀብቶች ናቸው” ...

Read More »

አቶ ሙራድ አብዱ አሊ በፕሬዚዳንትነት እንዲቀጥሉ ተወሰነ

አቶ ሙራድ አብዱ አሊ በፕሬዚዳንትነት እንዲቀጥሉ ተወሰነ ( ኢሳት ዜና መስከረም 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሃረሪ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ በቅርቡ የሃብሊ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ኦድሪን በድሪ አቶ ሙራድን ተክተው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲሰሩ ፍላጎት የነበረ ቢሆንም፣ የኦህዴድ የምክር ቤት አባላት አቶ ኦድሪን ለኦህዴድ ቀና አመለካከት የላቸውም በሚል በመቃወማቸው አቶ ሙራድ በስልጣን ላይ እንዲቀጥሉ ተደርጓል። ላለፉት 13 ዓመታት ...

Read More »

በዘጠኙ የዓየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጠ።

በዘጠኙ የዓየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ተሰጠ። ( ኢሳት ዜና መስከረም 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) የደመወዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው ነሃሴ 18 ቀን 2010 ዓ.ም ያቀረቡት ጥያቄን ተከትሎ የሥራ ማቆም አድማ ባደረጉት በዘጠኙ የዓየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ላይ መርማሪ ፖሊስ ያቀረበውን የ14 ቀናት የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ውድቅ በማድረግ ፍርድ ቤቱ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቀደ። መርማሪ ፖሊስ ...

Read More »