አቶ ሙራድ አብዱ አሊ በፕሬዚዳንትነት እንዲቀጥሉ ተወሰነ

አቶ ሙራድ አብዱ አሊ በፕሬዚዳንትነት እንዲቀጥሉ ተወሰነ
( ኢሳት ዜና መስከረም 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) የሃረሪ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ በቅርቡ የሃብሊ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ኦድሪን በድሪ አቶ ሙራድን ተክተው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲሰሩ ፍላጎት የነበረ ቢሆንም፣ የኦህዴድ የምክር ቤት አባላት አቶ ኦድሪን ለኦህዴድ ቀና አመለካከት የላቸውም በሚል በመቃወማቸው አቶ ሙራድ በስልጣን ላይ እንዲቀጥሉ ተደርጓል።
ላለፉት 13 ዓመታት ክልሉን የመሩት አቶ ሙራድ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው የምክር ቤት አባላት እንዳልተቀበሉዋቸውና ሰሞኑም ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረው ነበር። አቶ ሙራድ ተመልሰው የህባሊ ሊቀመንበር ይሁኑ አይሁኑ የታወቀ ነገር የለም።
በሌላ በኩል የሃብሊ ተወካዮች የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ከቄሮ ጋር በመወገን በመንግስት ላይ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገና እንዲዋቀር ጥያቄ አቅርበዋል።
ኦህዴዶች ደግሞ የክልሉ ሚዲያ በኦህዴድ አባላት እንዲመራ ያቀረቡትን ጥያቄ ሃብሊ ውድቅ አድርጎታል።