የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ኮፊ አናን የቀብር ስነስርዓት በተውልድ አገራቸው ተፈጸመ

የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የነበሩት ኮፊ አናን የቀብር ስነስርዓት በተውልድ አገራቸው ተፈጸመ
( ኢሳት ዜና መስከረም 03 ቀን 2011 ዓ/ም ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በዋና ጸሃፊነት የመሩት ጋናዊው ኮፊ አናን የቀብር ስነስርዓት የተለያዩ አገር መሪዎችና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በትውልድ አገራቸው ጋና መዲና አክራ ውስጥ ተፈጸመ።
ኮፊ አናን በተለያዩ የስልጣን እርከኖች አገራቸውን፣ አህጉራቸውን ጨምሮ ትልቁን ተቋም ተመድን ከመምራታቸውም በላይ የኖቤል ሰላም ሽልማት ተሸልመዋል።
በተወለዱ በ80 ዓመታቸው ባደረባቸው የልብ ሕመም በስዊዘርላንድ ያረፉት ኮፊ አናን አስመልክቶ የወቅቱ የተመድ ዋናጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ”አሁን ባለንበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ዓለማችን የሚያስፈልጋትን አንድ ታላቅ ሰው አጣች” ብለዋል።
በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያው ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመም መገኘታቸው ታውቋል።