መጋቢት ፲፰ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮ ፍሪ ኤሺያን በመጥቀስ ቢቢሲ እንደዘገበው፣መመሪያው መጀመሪያ የተላለፈው በዋና ከተማዋ በፒዮንግያንግ ከሁለት ሳምንት በፊት ነው። በአሁኑ ወቅት በ ሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በሙሉ አዋጁ ተግባራዊ እየሆነ መምጣቱን የዜና አውታሩ ጠቁሟል። በወጣት ፋሽን ተከታዮች “ስታይል” ጸጉራቸውን ከተቆረጡ የሰነበቱት ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን፤ ይባስ ብሎ ወንድ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችም እንደ እርሳቸው እንዲቆረጡ ...
Read More »በኦሮምያ ክልል በጉጂ ዞን የተፈጠረው ግጭት
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጋቢት 16፣ 2006 ዓም ከጉጂ ዞን ዋና ከተማ ስያሜ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ግጭት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች እንደሞቱ የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ግጭቱ የጉጅ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው ነገሌ ቦረና ፣ ነገሌ ብቻ ተብላ እንድትጠራ የመንግስት ባለስልጣናት ውሳኔ ማሳለፋቸውን ተከትሎ የቦረና ተወላጆች ተቃውሞ በማስነሳታቸው መነሳቱ ታውቋል። የቦረና ተወላጆች ታሪካዊቷ የነገሌ ቦረና ...
Read More »የጫፌ ኦሮምያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጨፌ ኦሮምያ ትናንት የጀመረውን የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ ሲያጠናቀቅ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትር የሆኑትን አቶ ሙክታር ከድርን በፕሬዚዳንትነት፣ እንዲሁም አቶ ለማ መገርሳን በአፈ ጉባኤነት መርጧል። ምንም አይነት ተወዳዳሪ እጩ ባልቀረበበት የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ድምጽ ሳይሰማ ፕሬዚዳንቱም አፈ ጉባኤውም ተመርጠዋል። ሌሎች የምክር ቤት አባላት አፈ ጉባኤው የፕሬዚዳንቱን ስም ጠርተው እንዲያጸድቁ ...
Read More »የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ቀጣይ የተቃውሞ መርሃግብር
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 2 አመታት ሲካሄድ የቆየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አርብ እንደሚጀመር ታውቋል። የተቃውሞ መሪ መፈክሩ “ሰላታችንን በመስኪዳችን” የሚል እንደሆነና መስኪዶችን በመንግስት ታማኞች ለማስያዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም አላማ ያደረገ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ሂደት ዛሬ ተጀምሯል። ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት ...
Read More »የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ዳግም ቃጠሎ
መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማተሚያ ቤቱ የወረቀት ክምችት መጋዘን ላይ መጋቢት 13 ቀን 2006 ዓ.ም ከሰዓት በሃላ በተነሳ ድንገተኛ የእሳት አደጋ መጋዘኑን የጎዳ ሲሆን ትናንት ጠዋት ደግሞ በዚሁ መጋዘን ላይ ተመሳሳይ አደጋ አጋጥሞአል፡፡ የመጀመሪያው አደጋ በማተሚያ ቤቱ የወረቀት ክምችት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በትናንትናው ዕለትም ተመሳሳይ አደጋ በተመሳሳይ ቦታ ላይ በማጋጠሙ ፣በማተሚያ ቤቱ የማሽን ...
Read More »በመርዓዊ ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናትና አርሶደአሮች ታሰሩ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን በሜጫ ወረዳ በእናሸንፋለን ቀበሌ በጨቦች ጎጥ ለአበባ ምርት በሚል የከርሰ ምድር ውሃ ለማውጣት መንግስት እንቅስቃሴ መጀመሩን የተቃወሙ ቁጥራቸው ከ200 እስከ 300 የሚደርስ አርሶ አደሮች፣ እድማያቸው ከ9 እስካ 12 የሚደርስ ታዳጊዎች፣ ሴቶችና ወጣቶች በገፍ ተይዘው በመርዓዊ ከተማ እና በዱርቤቴ እስር ቤቶች መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ባለፈው ሃሙስ ፕሮጀክቱን የተቃወሙ አርሶደሮች ...
Read More »በሻኪሶ ከ200 በላይ የኦሮሞ ተወላጆች ታስረዋል ሲል አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ ሊግ አስታወቀ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ በደቡብ ኦሮምያ በጉጂ ዞን በሻኪሶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ቁጥራቸው 200 የሚጠጋ ተማሪዎች በአዶላ ከተማ መታሰራቸውን ገልጿል። ብዙዎቹ ወጣቶች ከጸጥታ ሃይሎች በተተኮሰ ጥይት እና ድብደባ መቁሰላቸውን ሊጉ ገልጿል። የጸጥታ ሃይሎች የወሰዱት እርምጃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የገለጸው ሊጉ መንግስት እስረኞችን እንዲፈታ፣ ለቆሰሉት አስፈላጊው የህክምና ...
Read More »የጨፌ ኦሮምያ የክልሉን መሪ ይመርጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ሲጀመር ባለፉት ተከታታይ ቀናት ለውይይት ቀርቦ የነበረውን ሪፖርት ያለምንም ተቃውሞ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሞት የተለዩትን የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳን ለመተካት አዲስ ፕሬዚዳንት የሚመርጥ ሲሆን፣ ካፒታል የተባለው በአገር ውስጥ የሚታተመው የእንግሊዝኛ ጋዜጣ ቀድም ብሎ በሰበር ዜና የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ አስቴር ማሞ ፕሬዚዳንት ሆነው እንደሚሾሙ ...
Read More »የሃረሪ ሬዲዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም አዘጋጅ ታሰረ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ ጀማል ዳውድ ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ የታወቀ ሲሆን፣ ለእስር የዳረገውም መልእክቶችን በሞባይል ስልክ ልኸሃል ተብሎ ነው። ይሁን እንጅ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ሰዎች እንደገለጹት ጋዜጠኛ ጀማል የታሰረው በክልሉ ውስጥ የሚታየውን ዘረኝነት አጥብቆ በመቃወሙና ሌሎችን ጋዜጠኞች ታነሳሳለህ ተብሎ ነው። የክልሉ ፖሊስ አደገኛ መረጃዎችን በማሰራጨትና የተዛባ ዜና በመጻፍ ወንጀል ለመክሰስ ...
Read More »በሶማሊ ክልል ከ400 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር ሲወጣ ተያዘ
መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የደረሰው ዜና እንደሚያመለክተው ባለፈው ሳምንት ውጫሌ በሚባለው የጠረፍ ከተማ ላይ ከ400 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ በአይሲዙ መኪና ተጭኖ በህገወጥ መንገድ ሲወጣ በፌደራል ፖሊሶች ተይዟል። ሾፌሩና እና አብረው የነበሩ ሰዎች መጥፋታቸው ሲታወቅ ሁለት የፌደራል ፖሊሶች ገንዘቡን ለፌደራል መንግስት ለማስረከብ ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸው ታውቋል። ገንዘቡ የማን እንደሆነ ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
Read More »