የኬንያ መንግስት በአገሪቱ የሚገኙ የሶማሊያ ስደተኞች ወደ ካምፖች እንዲገቡ አዘዘ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኬንያ ይህን ህግ ያወጣችው የሶማሊያ ስደተኖች የጸጥታ ችግር ፈጥረውብኛል በሚል ነው። ሁሉም የሶማሊያ ስደተኞች ካኩማ እና ደደሃብ ወደሚባሉት የስደተኞች ካምፖች እንዲገቡ ይህን ባማያደረጉ ስደተኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መንግስት ገልጿል። አለማቀፍ ተቋማት ተቃውሞቸውን እየገለጹ ቢሆንም፣ የኬንያ መንግስት ግን በውሳኔው ለመጽናት የቆረጠ ይመስላል። በኬንያ በአልሸባብ የሚቀነባበሩ ፍንዳታዎች የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ ይታወቃል። አገሪቱ ...

Read More »

ለገጠሩ ወጣት የምንሰጠው መሬት ባለመኖሩ እየተሰደደ ነው ሲሉ አቶ ሃለማርያም ተናገሩ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ይህን ያሉት ኢህአዴግ የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዳራሽ በገመገመበት ወቅት ነው። ስራ ፈጠራውም ሆነ ሳይታረሱ የኖሩትን ወል መሬቶችን እያደራጁ ለወጣቱ አርሶደአር መስጠት አላዋጣም ያሉት አቶ ሃይለ ማርያም ፣ በገጠር መሬት የማከፋፈል ስራ ከተሰራ በሁዋላ የምንሰጠው መሬት በማጣታችን ስራ ካገኘው  ይልቅ የተሰደደው ወጣት ይበልጣል ብለዋል፡፡ አቶ ...

Read More »

መንግስት በእስልምና ትምህርት ቤቶች ውስጥ ህገመንግስት ለማስተማር ሞክሮ እንደነበር ገለጸ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤት ለዲፕሎማቶች እና ለሚኒስትሮች በተሰጠው ስልጠና ላይ እንደተገለፀው እስላማዊው መጅሊስ እራሱን የመምራት አቅም አልነበረውም ተብሎአል፡፡ ቀድሞ የነበረው መጅሊስ ሰነፍ የነበረና የራሱን ትምህርት ቤት ለመምራት ብቃት ያለነበረው ነው ያሉት የመንግስት ከፍተኛው ባለስልጣን፣ መጅሊሱ ብዙ ስህተቶችን ፈጽሟል ብለዋል። መጅሊሱ ያስመጣቸው የተለያዩ የውጭ ሰዎች ማስተማር ሲጀምሩ ወጣት ኢስላሚስቶቹ ተንጫጩ ያሉት ...

Read More »

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ልማት ሕዝብን ተጠቃሚ የማድረጉ ጉዳይ በሕዝብ ጥያቄ እንደተነሳበት አንድ ጥናት አመለከተ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በአዋጅ በፈረሰ ስያሜ የሚጠቀመው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት አዲስአበባን ጨምሮ በ20 ከተሞች አደረግነው ባሉት ጥናት በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው ልማት አብዛኛውን ሕዝብ ተጠቃሚ የማድረጉ ጉዳይ ሙሉ በሙሉ እምነት አለኝ ያለው ሕዝብ እጅግ አነስተኛ መሆኑን አመለከቱ፡፡ አዲስ ዘመን ጋዜጣ በትላንትና ዕትም የፊት ገጽ ላይ “ዜጎች የኢኮኖሚ ዕድገቱ በመንግስትና ሕዝብ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በውጭና በአገር ውስጥ የሚገኙ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ይሰልላል ተባለ

መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞችን ይሰልላል ብሎአል። ድርጅቱ ባወጣው ባለ 100 ገጽ ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለስርአቱ አደገኛ ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን  በውጭና በአገር ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎችን ለመሰለል ከተለያዩ አገሮች ቴክኖሎጂዎችን ማስገባቱን ” ገልጿል። የመንግስት ድርጊት ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ በነጻነት ...

Read More »

ኢትዮጵያ አሰብን ለማለፍ ስትል ከመቀሌ ታጁራ ለሚሰራው የባቡር መስመር ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ብር እንደምታወጣ ታወቀ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መቀሌ/ ወልድያ፣ ሰመራ ታጁራ የሚባለውን የባቡር ሃዲድ ፕሮጀክት ግንባታን ለመስራት ኢትዮጵያ 34 ቢሊዮን ብር የሚሆን ገንዘብ የመደበች ሲሆን ፣ መስመሩ አሰብን ለማለፍ ሲባል ተጨማሪ 6 ቢሊዮን ብር ወይም 300 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስወጣት ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። አገሪቱ ይህን ያክል ገንዘብ ለመክፈል የተገደደችው ባበሩ የሚያልፍበትን የተወሰነ የአሰብ አካባቢ ሳይነካ ለማሳለፍ በመገደዱዋ ነው። ...

Read More »

ኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃን በማዳረስ በኩል የሚሊኒየም ግቦችን ብታሳካም በንጽህና በኩል ወደ ሁዋላ መቅረቷን ዩኒሴፍ ገለጸ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ አመታዊውን የውሃ ቀን በማስመልከት ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ በሚሊኒየም የልማት ግቦች የተቀመጠውን ለ62 በመቶ የሚሆነው ህዝብ እስከሚቀጥለው አመት የንጹህ የመጠጥ ውሃ  ተጠቃሚ የማድረጉን እቅድ ተሳካለች። ይሁን እንጅ ይላል ድርጅቱ ህዝቡ ንጹህ መጸዳጃዎችን እንዲያገኝ በማድረግ በኩል አገሪቱ በእጅጉ ወደ ሁዋላ ቀርታለች። የሚሊኒየም የልማት ግቡ 51 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ንጹፍ መጸዳጃ እንዲያገኝ ...

Read More »

በጅጅጋ አንድ የልዩ ሃይል አባል የዩኒቨርስቲ ተማሪ ገጭቶ በመግደል አመለጠ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነውና ስሙ ለጊዜው ያልታወቀው ወጣት የተገደለው ጧት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አስቀድሶ ሲመለስ ነው። የልዩ ሃይል ንብረት የሆነችውን መኪና የሚያሽከረክረው ሰው ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ በፍጥነት በማሽከርከር ተሰውሯል። ልዩ ሚሊሺያው ሆን ብሎ ይግጨው ወይም በድንገት በተፈጠረ አደጋ ባይታወቅም፣ አደጋውን ከፈጸመ በሁዋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ማምለጡ የአካባቢውን ሰው አስቆጥቷል። ከሶስት ቀናት በፊትም እንዲሁም ...

Read More »

በሻኪሶ ተነስቶ ለነበረበው ብጥብጥ ህዝቡ መንግስትን ተጠያቂ እያደረገ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአስር ቀናት በፊት በሻኪሶ ከተማ ጎሳን ማእከል አድርጎ በተማሪዎች መካከል በተነሳው ብጥብጥ የመንግስት ባለስልጣናት እጅ አለበት ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የከተማው ባለስልጣናት በግጭቱ ዙሪያ ህዝቡን በማወያየት ላይ ሲሆኑ፣ የከተማው ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ለሚነሳው ግጭት የአካባቢው አስተዳዳሪዎች እጅ አለበት ማለታቸውን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ለኢሳት ገልጸዋል። ከተማዋ መረጋጋት ቢታይባትም፣ ተመሳሳይ ችግር ሊከሰት ...

Read More »

ከሳውዲ አረቢያ የተመሰሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተመልሰው እየተሰደዱ ነው

መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በአስከፊ ሁኔታ ከሳውድ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ዜጎች ተመልሰው እየተሰደዱ እንደሆን መረጃዎች አመለከቱ። ኢትዮጵያውያውያኑ ስደትን እንደ አማራጭ የሚጠቀሙበት በአገራቸው ለመስራት ሁኔታዎች እንዳልተመቻቹላቸው በመግልጽ ነው። በተለይ ወደ ትግራይና አማራ ክልሎች እንዲሄዱ የተደረጉ ስደተኞች በሁመራ በኩል ወደ ሱዳን በብዛት እየጎረፉ መሆኑን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ። አንዳንድ ወጣቶች ከሳውድ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለቀን ...

Read More »