በጅጅጋ አንድ የልዩ ሃይል አባል የዩኒቨርስቲ ተማሪ ገጭቶ በመግደል አመለጠ

መጋቢት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጅጅጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነውና ስሙ ለጊዜው ያልታወቀው ወጣት የተገደለው ጧት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን አስቀድሶ ሲመለስ ነው።

የልዩ ሃይል ንብረት የሆነችውን መኪና የሚያሽከረክረው ሰው ግድያውን ከፈጸመ በሁዋላ በፍጥነት በማሽከርከር ተሰውሯል። ልዩ ሚሊሺያው ሆን ብሎ ይግጨው ወይም በድንገት በተፈጠረ አደጋ ባይታወቅም፣ አደጋውን ከፈጸመ በሁዋላ ምንም እንዳልተፈጠረ ማምለጡ የአካባቢውን ሰው አስቆጥቷል።

ከሶስት ቀናት በፊትም እንዲሁም አንድ የፖሊስ መኪና ሶስት ባጃጆችን ገጭቶ ማመለጡን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ጉዳዩን በተመለከተ የከተማውን ፖሊስ ለማናገር ያደረገነው ጥረት አልተሳካም።