የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ቀጣይ የተቃውሞ መርሃግብር

መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት 2 አመታት ሲካሄድ የቆየው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አርብ እንደሚጀመር ታውቋል። የተቃውሞ መሪ መፈክሩ “ሰላታችንን በመስኪዳችን” የሚል እንደሆነና መስኪዶችን በመንግስት ታማኞች ለማስያዝ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም አላማ ያደረገ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ሂደት ዛሬ ተጀምሯል። ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለማሰማት በተገኙበት ወቅት የማህልና የቀኝ ዳኞች ተቀይረው በአዲስ ተተክተው አግኝተዋቸዋል።
የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የሚካሄደው የፍርድ ሂደት ፖለቲካዊ ይዘት ያለውና ነጻ አይደለም በማለት ውድቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።