በሶማሊ ክልል ከ400 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ከአገር ሲወጣ ተያዘ

መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የደረሰው ዜና እንደሚያመለክተው ባለፈው ሳምንት ውጫሌ በሚባለው የጠረፍ ከተማ ላይ ከ400 ሺ ዶላር በላይ ገንዘብ በአይሲዙ መኪና ተጭኖ በህገወጥ መንገድ ሲወጣ በፌደራል ፖሊሶች ተይዟል።

ሾፌሩና እና አብረው የነበሩ ሰዎች መጥፋታቸው ሲታወቅ ሁለት የፌደራል ፖሊሶች ገንዘቡን ለፌደራል መንግስት ለማስረከብ ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸው ታውቋል።

ገንዘቡ የማን እንደሆነ ለማወቅ የተደረገው ጥረት አልተሳካም።