ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር ሰብአዊ መብት ድርጅት ከኢትዮጵያ ታስክ ፎርስ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያውያን ሰሞኑን በኦሮሞ፣ በአፋር፣ በጎንደር እና በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸሙት ግድያዎች በጽኑ አውግዘዋል። ከአስተባባሪዎች አንዱ ሆኑት ዶ/ር ኮንቴ የኢትዮጵያውያኑን ጥያቄ ለአውሮፓ ህብረት ባለስልጣናት ማቅረባቸውንና በሚቀጥለው ሳምንትም ከህብረቱ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ካተሪና አሽተን ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዙን ገልጸዋል። የአውሮፓ ህብረት ...
Read More »የሜሪሲ የውሃ ፕሮጀክት በሙስና ምክንያት ቆመ
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ የትውልድ ከተማ ላይ 62 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የውሃ ፕሮጀክት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ በመክሸፉ የፕሮጀክቱ ማናጀርና የገንዘብ ቤት ሃላፊው በቁጥጥር ስር ውለዋል። የዚህ ፕሮጀክት ዋና ተጠያቄ የውሃ ቢሮ ሃላፊዋና ፕሮጀክቱን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው የልዩ ፖሊስ አዛዥና ፕሬዚዳንቱ የጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄኔራል አብዲ አደም መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል። ...
Read More »በሞያሌ በኦነግና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱ ታወቀ
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ በሞያሌ ገጠራማ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በኦነግ ወታደሮች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 2 የኦነግ ወታደሮች ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የመንግስት ወታደሮችም መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ሁለቱ የኦነግ ወታደሮች ቀኑን ሙሉ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተጥለው ይታዩ እንደነበር የአይን እማኖች ገልጸዋል። 4 የመንግስት ወታደሮች በጽኑ ቆስለው ህክምና ሲደረግላቸው እንደነበር የአይን እማኞች አክለው ተናግረዋል። የመንግስት ...
Read More »በቦዴዎችና ኮንሶዎች ማካከል ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው
ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትንናት ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በጊዮ ሰፈራ ጠባያ ቦዲዎች ባደረሱት ጥቃት አንድ የኮንሶ ተወላጅ ሲገደል በሰላማጎ ወረዳ ዋና ከተማ ሃና ላይ ደግሞ 2 ሴቶች ቆስለው በጅንካ ሆስፒታል እየታከሙ ነው። አሰበች ጠጉ የተባለች የ4 ልጆች እናት ክፉኛ የቆሰለች ሲሆን፣ ባለቤቷ በእስር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ልጆቿ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል። ሌላዋ ቁስለኛ የስራ ...
Read More »ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር ድፍረቱ እንደሌላቸው አስታወቁ
ሚያዚያ ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድሬዳዋና በሃረር አብያተ ክርስቲያናትና በግለሰቦች ቤት ተጠግተው የሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚታየው ድባብ አስፈሪ መሆን ትምህርት በቶሎ ይጀመራል የሚለውን ተስፋ አጨልሞታል። መንግስት ውጥረቱ መርገቡን በመግለጽ ከግቢ የወጡ ተማሪዎች ተመልሰው እንዲገቡና ትምህርት እንዲጀምሩ ጥሪ ቢያቀርብም፣ አንዳንድ ግቢውን ጎብኝተው የተመለሱ ተማሪዎች ግን ሁኔታው አሁንም አስፈሪ በመሆኑ ትምህርት ለመጀመር ፍላጎት የለንም ብለዋል። አንድ ተማሪ ...
Read More »የህወሃት ደጋፊ ኦህዴዶች ከተቀረው የኢህዴድ አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸው ታወቀ
ሚያዚያ ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባና የዙሪያዋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የጋራ ልማት መሪ ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ሰሞኑን ከስድስት በላይ በሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች በተቀጣጠለው ተቃውሞ ምክንያት የኦሮሞ ተማሪዎች በአጋዚ ልዩ ኃይልና በፌዴራል ፖሊስ አባላት መገደላቸው ኦህዴድን ለሁለት ሊከፍል የሚችል ክስተት ሆኖ ብቅ ማለቱን ምንጮች ገልጸዋል። በኦህዴድ ድክመት ምክንያት ስለማስተር ፕላኑ አስቀድሞ ሕዝቡ ተወያይቶበት ውሳኔ ሳይሰጥበት ወደ ...
Read More »ዞን ዘጠኝ እየተባሉ የሚጠሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች በአሸባሪነት ሊከሰሱ መሆኑ ታወቀ
ሚያዚያ ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው የ10 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ፣ ጋዜጠኛ አስማማው ሃይለጊዮርጊስ፣ ጸሃፊ ዘላለም ክበረት፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃነና ኤዶም ካሳየ አርቲክል 19 እየተባለ ከሚጠራው ይውች ድርጅት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የግብጽ፣ የኤርትራ መንግስትንና የግንቦት7 ትን ተልእኮ ለማስፈጸም ይንቀሳቀሱ ነበር የሚል ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል። መንግስት ወጣቶቹ ...
Read More »በአምቦ ለደረሰው የሰው እልቂትና የንብረት ውድመት መንግስት ራሱን ነጻ ለማድረግ ዘመቻ ጀመረ
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም በአምቦና አካባቢው በሚገኙ ከተሞች ወደ አደባባይ የወጡትን ከ40 በላይ ንጹሃን ዜጎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ያስገደለው መንግስት ራሱን ከተጠያቂነት ለማዳን የጀመረውን ፕሮፓጋንዳ በስፍራው ላይ የነበሩ አንዳንድ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተቃውመውታል። አፈ ጉባኤ አባ ዱላ ገመዳ በኢቲቪ ቀርበው የተማሪዎችን ጥያቄ ኦነግ እና ግንቦት7 የተባሉት አሸባሪ ቡድኖች አይዟችሁ በማለት አቀጣጥለውታል ...
Read More »የመንግስት ካድሬዎች በኦሮምያ የተነሳውን ግጭት የብሄር ግጭት ለማስመሰል ዘመቻ መጀመራቸው ታወቀ።
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከኦህዴድ ምንጮች ባገኘው መረጃ ተንተርሶ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በአማራና በኦሮሞ ህዝብ መካከል ልዩነትን በመዝራት ሁለቱን ታላላቅ ብሄሮች ለማጋጨት ያቀዱትን ሴራ ይፋ ካደረገ በሁዋላ፣ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተሰማሩ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች የአማራና ኦሮሞ ወጣቶች እንዲጋጩ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በሃሮማያ እና በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲዎች አንዱን ብሄር የሚያጥላሉ ንግግሮች ሆን ተብሎ ተልእኮ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞና ጸሃፊዎች መታሰር እንዳሳሰበው ገለጸ
ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በካተሪና አሽተን የሚመራው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ክፍል በጋዜጠኞች ፣ ጸሃፊዎችና ፖለቲከኞች ላይ እየተካሄደ ያለው እስር እንዳሳሰበው ገልጿል። የአውሮፓ ህብረት ሁሉንም ወገኖች ያቀፈ ውይይት እንዲደረግ እና የተለያዩ ድምጾች የሚሰሙበት መድረክ እንዲፈጠር ጠይቋል። ህብረቱ የጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች መታሰር እንዳሳሰበው ከመግለጽ በተጨማሪ ጉዳያቸው በነጻ ፍርድ ቤት እንዲታይ፣ ተጠርጣሪዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት መንገድ እንዲመቻችላቸው ጠይቋል። ተጠርጣሪዎቹ ...
Read More »