በሞያሌ በኦነግና በመከላከያ ሰራዊት መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱ ታወቀ

ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሰኞ በሞያሌ ገጠራማ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በኦነግ ወታደሮች መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 2 የኦነግ ወታደሮች ሲሞቱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የመንግስት ወታደሮችም መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ሁለቱ የኦነግ ወታደሮች ቀኑን ሙሉ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ተጥለው ይታዩ እንደነበር የአይን እማኖች ገልጸዋል። 4 የመንግስት ወታደሮች በጽኑ ቆስለው ህክምና ሲደረግላቸው እንደነበር የአይን እማኞች አክለው ተናግረዋል። የመንግስት ወታደሮች በእነሱ በኩል የሞቱትን የሚደብቁ በመሆኑ ቁጥሩን በትክክል ለማወቅ አለመቻላቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ብዙ የመንግስት ወታደሮች እንደተገደሉ እየተወራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከመንግስት በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም።