የሜሪሲ የውሃ ፕሮጀክት በሙስና ምክንያት ቆመ

ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ  የትውልድ ከተማ ላይ 62 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የውሃ ፕሮጀክት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ በመክሸፉ የፕሮጀክቱ ማናጀርና የገንዘብ ቤት ሃላፊው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የዚህ ፕሮጀክት ዋና ተጠያቄ የውሃ ቢሮ ሃላፊዋና ፕሮጀክቱን በበላይነት እንዲቆጣጠሩ ሃላፊነት የተሰጣቸው  የልዩ ፖሊስ አዛዥና ፕሬዚዳንቱ የጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄኔራል አብዲ አደም መሆናቸውን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱን ገንዘብ  ባለስልጣኖቹ ለራሳቸውን ጥቅም በማዋላቸው ሳይሳካ መቅረቱን ተከትሎ፣  ባለስልጣኖቹ ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን ኢንጂነር አንተነህ ከተማና የሂሳብ ሰራተኛው ያሲን ዚያድ እንዲታሰሩ መደረጉን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት ምንጮች አክለው ገልጸዋል። ጉዳዩን በማስመልከት የክልሉን የውሃ ቢሮ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።