በቦዴዎችና ኮንሶዎች ማካከል ያለው ግጭት እንደቀጠለ ነው

ግንቦት ፩ (አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ትንናት ከምሽቱ አንድ ሰአት ላይ በጊዮ ሰፈራ ጠባያ ቦዲዎች ባደረሱት ጥቃት አንድ የኮንሶ ተወላጅ ሲገደል  በሰላማጎ ወረዳ ዋና ከተማ ሃና ላይ ደግሞ 2 ሴቶች ቆስለው በጅንካ ሆስፒታል እየታከሙ ነው።

አሰበች ጠጉ የተባለች የ4 ልጆች እናት ክፉኛ የቆሰለች ሲሆን፣ ባለቤቷ በእስር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ልጆቿ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሎአል።

ሌላዋ ቁስለኛ የስራ ኤፍሬም ግራ ጭኗ ላይ በጥይት በመመታቱዋ ጊዚያዊ ህክምና እየተደረገላት ነው።

መንግስት ለሸንኮራ አገዳ ልማት በሚል ኮንሶዎችን በማፈናቀልና በቦዲዎች አካባቢ ከማስፈሩ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተደጋጋሚ ግጭት ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰዎች አልቀዋል።

በአካባቢው የተሰማራው የፌደራል ፖሊስ በሚወስደው እርምጃም እንዲሁ ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰዎች እየተጎዱ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።