ከሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የወጡ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር ድፍረቱ እንደሌላቸው አስታወቁ

ሚያዚያ ፴ (ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በድሬዳዋና በሃረር አብያተ ክርስቲያናትና በግለሰቦች ቤት ተጠግተው የሚገኙ ተማሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሚታየው ድባብ አስፈሪ መሆን ትምህርት በቶሎ ይጀመራል የሚለውን ተስፋ አጨልሞታል። መንግስት ውጥረቱ መርገቡን በመግለጽ ከግቢ የወጡ ተማሪዎች ተመልሰው እንዲገቡና ትምህርት እንዲጀምሩ ጥሪ ቢያቀርብም፣ አንዳንድ ግቢውን ጎብኝተው የተመለሱ ተማሪዎች ግን ሁኔታው አሁንም አስፈሪ በመሆኑ ትምህርት ለመጀመር ፍላጎት የለንም ብለዋል።

አንድ ተማሪ ” በተማሪዎች መካከል መተማመን በመጥፋቱ ፣ በውጭ ያሉ ተማሪዎች ዶክመንታቸውንና ልብሶቻቸውን ይዘው ወደ አካባቢያቸው ከመመለስ ውጭ የመማር ፍላጎት የላቸውም” ብሎአል።

በሌላ በኩል ደግሞ በኦሮምያ ክልል የህወሃትና የኦህዴድ ካድሬዎች እየነዙት ያለው በአንድ ብሄር ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ዘመቻ ያሰጋቸው አንዳንድ ኢትዮጵያውያን፣ ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርግ እየመከሩ ነው።

በተመሳሳይ ዜናም ሰማያዊ ፓርቲ ” ኢትዮጵያውያንገዥውፓርቲበፈጠረውየከፋፍለህግዛስርዓትሳይወናበዱበዜጎቻችንላይየሚደርሰውንህገወጥእርምጃ ላይ ድምጻቸውንእንዲያሰሙናለስርዓቱመሳሪያከመሆንእንዲቆጠቡ” ጠይቋል።

“የዜጎችንጥያቄበግድያማስቆምአይቻልም” በሚል ርእስ መግለጫ ያወጣው ሰማያዊ ፓርቲ፣ በአሁኑወቅትኢትዮጵያነጻእንዲወጡእገዛያደረገችላቸውንጨምሮአብዛኛዎቹአገራትየህዝብንጥያቄበተገቢውየሚያዳምጡ፣ችግሮችሲኖሩበጠረጴዛዙሪያናበሰከነመልኩመፍታትየሚችልመንግስትመመስረትሲችሉበተቃራኒውበአገራችንስልጣንላይያለውህወሓት/ኢህአዴግግንዜጎችንበኃይልእየገዛ” እንደሚገኝ፣  በቅርቡበአገሪቱየተለያዩክፍሎችየተፈጸሙትንግድያዎችናሌሎችህገወጥእርምጃዎችበምሳሌነትበማንሳት ጠቅሷል።

ፓርቲው  ” የአዲስአበባናበዙሪያዋየሚገኙትከተሞች ‹‹የተቀናጀመሪፕላን ›› አስመልክቶበስርዓቱላይጥርጣሬየገባቸውየዩኒቨርሲቲተማሪዎችያነሱትሰላማዊጥያቄተከትሎበርካታተማሪዎችናነዋሪዎችህይወታቸውንማጣታቸውን ፣ መቁሰላቸውንና መታሰራቸውን፣ ከወራትበፊትበሀረርከተማየተከሰተውንቃጠሎተከትሎምዜጎችላይተመሳሳይእርምጃመወሰዱን፣  በባህርዳርናጎንደርከተሞች ‹‹ህገወጥግንባታነው›› ተብለውያለካሳ፣ቅያሬናበቂጊዜቤታቸውየፈረሰባቸውዜጎችቤታቸውበዚህሁኔታመፍረሱአግባብአለመሆኑንበመግለጻቸውበጥይትመደብደባቸውን፣በተለይምጥያቄያነሳሉተብለውየተፈሩትአባወራዎችእስርቤትውስጥመታጎራቸውን ” አውስቷል።

“ዜጎችጥያቄያችውምንምይሁንምን ‹‹መንግስትነኝ!›› ብሎስልጣንላይየተቀመጠአካልጥያቄያቸውንአዳምጦበሰከነመንገድምላሽወይንምመፍትሄየመስጠትግዴትየነበረበትቢሆንም፣ገዥውፓርቲ ግን ምላሹ  ጥይት ነው” ሲል ኮንኗል።

ፓርቲው በመያያዝም ገዥውፓርቲየዜጎችንጥያቄበኃይልለማፈንየሚሞክረውለዜጎችመሰረታዊጥያቄንአሟልቶአገርየመምራትብቃትየሌለውከመሆኑአንጻርህዝብሌሎችበርካታጥያቄዎችንያነሳብኛልብሎስለሚሰጋ፣የተነሱትንምጥያቄዎችየመመለስአቅምስለሌለውናምንምአይነትችግርቢኖርምህዝብእያስፈራራለመግዛትካለውአባዜየሚነሳ መሆኑን ጠቅሷል።

አገራችንከመቼውምጊዜበላይወደበፖሊስመንግስትነት መለወጡዋን የሚጠቅሰው ሰማያዊ ፓርቲ፣  ኢትዮጵያዜጎችሰላማዊጥያቄያቸውንለመንግስትየማያቀርቡባት፣ጥያቄያቸውንሲያቀርቡምህይወታቸውንየሚያጡባትአገርእንደሆችየሰሞኑአረመኔያዊእርምጃ ማሳያ መሆኑን ገልጿል።

ገዥውፓርቲበኢትዮጵያውያንላይየወሰደውንእርምጃህጋዊለማስመሰልየባንክዘረፋንናህገወጥየቤትግንባታንየመሳሰሉትንምክንያቶችበመጥቀስየተወሰደውንእርምጃህጋዊለማድረግመሞከሩምተጠያቂነትየጎደለውናከምክንያትየራቀበመሆኑ፤እነዚህዜጎችላይየተወሰደውንእርምጃላይለህዝብበቂመረጃእንዲሰጥናተጠያቂነቱንእንዲወስድም አሳስቧል፡፡ዜጎች ህወሓት/ኢህአዴግበፈጠረውየከፋፍለህግዛስርዓትሳይወናበዱበዜጎቻችንላይየሚደርሰውንህገወጥእርምጃላይድምጻቸውንእንዲያሰሙናለስርዓቱመሳሪያከመሆንእንዲቆጠቡእንዲሁምአገርበቀልናዓለምአቀፍየሰብአዊመብትተቋማት፣የሚዲያተቋማት፣የፖለቲካድርጅቶችናሚዲያዎችገዥውፓርቲበህዝብላይእየወሰደውያለውንየኃይልእርምጃእንዲያጋልጡናእንዲቃወሙ፣እያጋለጡናእየተቃወሙያሉትምአጠናክረውእንዲቀጥሉሰማያዊፓርቲጥሪውን አቅርቧል።