በደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እየተዋከቡ መሆኑን ገለጹ

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳ የመንግስት ስልጣን በተቆናጠጡ የወረዳ ሹሞች በተደጋጋሚ የደረሰባቸው አስተዳደራዊ በደልና የሰብኣዊ መብት ጥሰት ወንጀል እንዲጣራና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ  አቤቱታ ያቀረቡ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አማሬ ቦሬና በ አቶ ጅሎ ቦነያ አማካይነት ያለአንዳች ምክንያት መታሰራቸውን፣ በእስር ወቅትም በተደጋጋሚ ደብደባ እንደተፈጸመባቸውና ይህን ለማጋለጥ ባደረጉት ...

Read More »

ለ70 አመታት ያገለገለው ድልድይ በጥናት ችግር ፈረሰ

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ደልጊ ፣ሻውራ፣ ጎርጎራና ቋራን ለ70 ዓመታት በማገናኘት ያገለገለው ድልድይ በመንገድ ስራ በተፈጠረ የጥናት ችግር ቢፈርስም ተመልሶ ሊሰራ ባለመቻሉ ከፍተኛ ችግር ደርሶብናል በማለት የጯሂት ከተማ ነዋሪዎች አማረዋል፡፡ ከጎንደር ወደ ጯሂት በሚወስደው መንገድ ላይ በጣልያን መንግስት እንደተሰራ የሚነገረው የሱዳን ገደል ድልድይ ከአራት ወራት በፊት በመፍረሱ  ወላዶች፣አረጋውያንና የንግዱ ማህበረሰብ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ...

Read More »

በ9 ወራት ብቻ ከ1 ሚሊዮን 800 ሺ በላይ ስራ አጦች ተመዘገቡ

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ዓመት በዘጠኝ ወራት ብቻ የሥራ ፈላጊዎችን መረጃ ለማጠናቀር ታስቦ በተካሄደ ምዝገባ በመላ ሀገሪቱ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሥራ ፈላጊዎች በፈቃደኝነት መመዝገባቸውንና ከነዚህ ውስጥ ከ351ሺህ በላይ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጆች ምሩቃን መሆናቸውን ከከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተገኘ ጥናት አመለከተ፡፡ ይህ ጉዳይ መጪው ምርጫ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል የገመተው ኢህአዴግ በተለይ በአዲስአበባ ባለፉት ...

Read More »

መንግስት በደቡብ ኦሞ ዞን ለሚታየው ችግር መፍትሄ ለመስጠት አለመቻሉ አደጋውን አባብሶታል ታበለ

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት መሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ መኮንን ለኢሳት እንደገለጹት መንግስት ከጀመረው የሸንኮራ እርሻ ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ እየጠፋ ያለው ሰው ህይወት መንግስት መፍትሄ ሊሰጠው ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ነው። በጅንካ ነዋሪ የሆነው  ኡመር ንጋቱ  በሙርሲ ብሄረሰብ አባላት በጥይት ተደብድቦ እንደሞተ መነገሩን ተከትሎ ሃሙስ እለት ከቀብር መልስ የተቃውሞ ሰልፍ የተካሄደ ሲሆን፣ ከሰአት ...

Read More »

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከኢትዮጵያ ጋር የሚኖረው ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ

መስከረም ፲፮(አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋር የተገናኙነት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በሰላም ማስጠበቅና ሽብርተኝነትን በመዋጋት በኩል እያደረገች ያለውን ሚና አወድሰዋል። አገሪቱ በደቡብ ሱዳንና በሶማሊያ ሰላም በማስጠበቅ በኩለ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ኢትዮጵያ  የሰላም አስከባሪ በመላክ ቁጥር በአለም ግንባር ቀደም ከሆኑ መንግስታት ተርታ እንደምትመደብም ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ቦይንግ አውሮፕላን ለመግዛት ውል መፈጸሙ ...

Read More »

የጅንካ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን በጅንካ ከተማ በአይነቱ ልዩ ነው ተባለ የተቃውሞ ሰልፍ መደረጉን የአካባቢው ምንቾች ገልጸዋል። የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገው ከጅንካ ከተማ  ወደ ሃና በመጓዝ ላይ የነበረ አንድ ሰራተኛ መገደሉን ተከትሎ ነው። ሃና አዲሱ የስኳር ፋብሪካ ግንባታ የሚካሄድበት ቦታ ሲሆን፣ ግድያውን የፈጸሙትም የስኳር ልማቱ ከቀያቸው ያፈናቀላቸው የሙርሲ ብሄረሰብ አባላት ሳይሆኑ እንደማይቀር ይገመታል። የጅንካ ተወላጁ ...

Read More »

ጄ/ል አበባው ታደሰ መከላከያን ለቀቁ

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-98 በመቶ የሚሆነውን  የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የአዛዥነት ቦታዎችን ከተቆጣጠሩት የህወሃት ጄኔራሎች ባልተናነሰ  በከፍተኛ የስልጣን ቦታ ላይ የነበሩት ብቸኛው የአማራ ተወላጁ ጄኔራል አበባው ታደሰ በጄ/ል ሳሞራ የኑስ ትእዛዝ ከሃላፊነታቸው ዝቅ ብልው እንዲሰሩ ከተወሰነባቸው በሁዋላ በመጨረሻ ከመከላከያ ሰራዊት መሰናበታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። ጄ/ል አበባው ከጄ/ል ሞላ ሃ/ማርያም እና ከጄ/ል ሰአረ መኮንን ጋር በመነጋገር ጄ/ል ሳሞራ ...

Read More »

መንግስት አርሶ አደሩን እየከፋፈለው ነው ተባለ

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ አልተቀበሉም ባላቸው አርሶ አደሮች ላይ በይፋ የማሸማቀቅ ስራ እየሰራ መሆኑን አርሶ አደሮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። የገዢውን ፓርቲ ፖሊሶች ተቀብለው አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ አርሶአደሮች ” ታካች አርሶ አደር “የሚል ስያሜ እየተሰጣቸው በተለያዩ መንገዶች እየተዋከቡና በእዳ እየተጠየቁ ሲሆን፣ የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ አርሶአደሮች ደግሞ “ልማታዊ አርሶ አደር” ተብለው ይሞካሻሉ። ...

Read More »

ሀሰተኛ ብሮች በብዛት መሰራጨታቸው ታወቀ

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተሰራጩ ሲሆን፣ ፖሊስ በየቀኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ ቢችልም ችግሩ አሁንም በስፋት እየታየ ነው። የፌደራል ፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው በመላ አገሪቱ በተሰራጨው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሃሰት የብር ኖቶች መንግስት በየቀኑ ከባንኮችና ከገበያ ሱቆች ለመሰብሰብ ተገዷል። ፖሊስ በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተዋል ያላቸውን 58 ሰዎች ማሰሩን ቢያስታውቅም፣ ...

Read More »

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የፖለቲካ ስልጠናውን ተቀላቀሉ

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን የአብዮታዊ ዲሞክራሲ የትምህርት መመሪያን ለማጥመቅ ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ በአገሪቱ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስልጠናውን በግዳጅ እንዲወስዱ እየተደረጉ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎቹ የፖለቲካ ስልጠና እንዳለ አስቀድመው በመስማታቸው ፣ ከስልጠናውን የቀሩ ሲሆን፣ የገዢው ፓርቲ የወረዳ ሹሞች መምህራን ተማሪዎችን እንዲያመጡ የተለያዩ ዘዴዎችን እንዲጠቀሙ እያግባቡ ነው። አንድ መምህር ለኢሳት እንደገለጹት፣ ከተማሪዎች በፊት ...

Read More »