በደቡብ ክልል የተፈናቀሉ ነዋሪዎች እየተዋከቡ መሆኑን ገለጹ

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳ የመንግስት ስልጣን በተቆናጠጡ የወረዳ ሹሞች በተደጋጋሚ የደረሰባቸው አስተዳደራዊ በደልና የሰብኣዊ መብት ጥሰት ወንጀል እንዲጣራና በአጥፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ  አቤቱታ

ያቀረቡ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸውን ገልጸዋል። ከ1993 ዓ.ም ጀምሮ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ በአቶ አማሬ ቦሬና በ አቶ ጅሎ ቦነያ አማካይነት ያለአንዳች ምክንያት መታሰራቸውን፣ በእስር ወቅትም በተደጋጋሚ ደብደባ እንደተፈጸመባቸውና ይህን

ለማጋለጥ ባደረጉት እንቅስቃሴ ከመኖሪያ ቤታቸው ጭምር እንዲፈናቀሉ መደረጉን ነዋሪዎች አመልክተዋል፡፡ ይህ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ተጣርቶ እርምጃ እንዲወሰድ ከክልሉ ፕሬዚደንት ጨምሮ በየደረጃው ላሉ አካላት አቤቱታ በየጊዜው ቢያስገቡም አንድም

የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩን እንዳሳዘናቸው ለዘጋቢያችን  ተናግረዋል፡፡ በደል ደርሶብናል ያሉት 9 ያህል አመልካቾች ስለጉዳዩ ሲያስረዱ ከ1993 እስከ 2000 ዓ.ም የደረሰባቸውን በደል በቡርጂ ወረዳ ፖሊስ አቅርበው የነበረ ቢሆንም የምርመራ መዝገቡ

ለፍ/ቤት ሳይቀርብና ግለሰቦቹም በሕግ ሳይጠየቁ እስከአሁን ቆይቷል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት መንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት በሚል እስከ ቀበሌ ድረስ በተፈጠረው የህዝብ ውይይት መድረክ ቀደም ሲል በአካባቢው ባለሰልጣናት የደረሰብንን በደል አቅርበን እንዲታይ ተደርጎ አቤቱታችንን በጹሑፍ እንድናቀርብ

በጠየቅነው መሰረት ካቀረብን በሃላ ችግሩ ይፈታል ብለን ስንጠብቅ በተቃራኒው በደረሰብን ወከባና እንግልት አካባቢያችን ለቀን ለመውጣት አስገድዶናል ሲሉ አቤቱታቸውን አቅርበዋል፡፡

እንደአቤቱታ አቅራቢዎቹ ገለጻ ከሆነ የአካባቢው ባለስጣናት ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ የራሳቸውን ሕገወጥ የጥቅም ትስስር የዘረጉ መሆኑን ለአቤቱታ በተንከራተቱባቸው ጊዜያቶች ማረጋገጣቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡