የወግዲ ወረዳ መምህራን የስራ ማቆም አድማ አደረጉ

መስከረም ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ የመሰናዶ እና የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ መመህራን የስራ ማቆም አድማውን ያደረጉት መንግስት ቃል በገባው መሰረት የሃምሌ እና ነሃሴ ወር ደሞዝ ጭማሪ አልከፈለንም በሚል ነው።

መመህራኑ የደሞዝ ጭማሪው ከተገለጸበት ጊዜ አንስቶ በታየው የዋጋ ንረት እየተሰቃየን ነው በማለት የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አስተዳዳሪው ለስብሰባ በሜዳቸው ሳይሳካለቸው ቀርቷል። እርሳቸውን የወከሉት አቶ ሃጎስ የተባሉ ሰው

ከመምህራኑ ጋር ሃይለ ቃል መለዋወጣቸውን ተከትሎ መጠነኛ ውዝግብ መፈጠሩን ምንጮች ገልጸዋል። መምህራኑ ጭማሪው በአስቸኳይ ካልተከፈላቸው በአድማው እንደሚቀጥሉበት እየተናገሩ ነው።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ እንድሪስ ስብሰባ ላይ በመሆናቸው አስተያየታቸውን ለመስጠት እንደማይችሉ ተናግረዋል።