መንግስት አርሶ አደሩን እየከፋፈለው ነው ተባለ

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጂ አልተቀበሉም ባላቸው አርሶ አደሮች ላይ በይፋ የማሸማቀቅ ስራ እየሰራ መሆኑን አርሶ አደሮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።

የገዢውን ፓርቲ ፖሊሶች ተቀብለው አባል ለመሆን ፈቃደኛ ያልሆኑ አርሶአደሮች ” ታካች አርሶ አደር “የሚል ስያሜ እየተሰጣቸው በተለያዩ መንገዶች እየተዋከቡና በእዳ እየተጠየቁ ሲሆን፣ የስርአቱ ደጋፊ የሆኑ አርሶአደሮች ደግሞ “ልማታዊ

አርሶ አደር” ተብለው ይሞካሻሉ።

ታካች ተብለው የተሰየሙት አርሶደአሮች በስርአቱ ካድሬዎች በሚደርስባቸው ወከባና ጫና ልጆቻቸው ትምህርት ከማቋረጥ ጀምሮ በሰበብ አስባቡ እንዲታሰሩ እየተደረጉ ነው። በተለይ የተቃወሚ አባላት የሆኑ አርሶ አደሮች መጪውን

ምርጫ ተከትሎ እየደረሰባቸው ያለው እንግልት እየከፋ መሄዱን ዘጋቢያችን አክላ ገልጻለች። ኢህአዴግ ከአርሶአደሩ ከፍተኛ ድጋፍ እንዳለው በተደጋጋሚ ይገልጻል።