ሀሰተኛ ብሮች በብዛት መሰራጨታቸው ታወቀ

መስከረም ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተሰራጩ ሲሆን፣ ፖሊስ በየቀኑ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለመሰብሰብ ቢችልም ችግሩ አሁንም በስፋት እየታየ ነው።

የፌደራል ፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው በመላ አገሪቱ በተሰራጨው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሃሰት የብር ኖቶች መንግስት በየቀኑ ከባንኮችና ከገበያ ሱቆች ለመሰብሰብ ተገዷል።

ፖሊስ በዚህ ስራ ላይ ተሰማርተዋል ያላቸውን 58 ሰዎች ማሰሩን ቢያስታውቅም፣ ገንዘቡ የሚሰራጭበትን ቦታ ለማወቅ አልቻለም።