ኢህአዴግ ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀርብበትም ለህዝቡ የሚሰጠውን የግዳጅ የፖለቲካ ስልጠና ቀጥሎበታል

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በሚያደርገው ዝግጀቱ የመንግስት ሰራተኞችን፣ መመህራንና ተማሪዎችን በማስገደድ የሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና እንደቀጠለ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንትም በርካታ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጥያቄዎች ተነስተዋል። በአዲስ አበባ በኢትዮ-ቻይና ቲቪቲ በነበረው ስልጠና ላይ ” ከ23 አመታት በሁዋላ አሁንም እራሳችሁን ከደርግ ጋር እያነጻጸራችሁ ነው? ደርግ ከሻእቢያ፣ ከእናንተ ጋርና ከሶማሊያ ጋር ጦርነት ውስጥ ሆኖ የቴክኒክና የንድፈሃሳብ ማሰልጠኛዎችን ...

Read More »

በጋምቤላ ግጭት እንደገና ማገርሸቱ ተሰማ

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ለቀናት ጋብ ብሎ የቆየው ግጭት ከትናንት ጀምሮ እንደገና አገርሽቷል። የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ጋትሉዋክ ቱት የገዢው ፓርቲ ልሳን ለሆነው ፋና ሬዲዮ ” ኪራይ ሰብሳቢዎችና የመሬት ደላሎች በጠነሰሱት ሴራ ለዘመናት ተቻችሎ የኖረውን ህዝብ ለመከፋፈል ጥረት በማድረጋቸው መስከረም አንድ በሚጤ ከተማ በተፈጠረው ግጭት 13 ሰዎች” መሞታቸውን፣ በገጠር ቀበሌዎችም ተመሳሳይ ግጭት ተከስቶ ቁጥሩ ...

Read More »

ለመምህራን ተማሪዎች በሚሰጠው የፖለቲካ ስልጠና ምክንያት የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ ተራዘመ

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመላ አገሪቱ የሚገኙ የትምህርት ተቋማት መስከረም 5 ትምህርት እንዲጀምሩ ቀደም ብሎ ይዞት የነበረውን እቅድ በመሰረዝ አዲሱ የትምህርት ዘመን ከመስከረም 30 በሁዋላ እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላልፏል። በትምህርት ሚ/ር ደኤታ ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ ዲንሳ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች መስከረም 5፣ 2007 ዓም የተጻፈው ደብዳቤ   የአንደኛ አመት ወይም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ ተደርጎ ከመስከረም 18 -20/2007 ዓም ምዝገባ ...

Read More »

ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጉዋን፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለማፈን መጠቀሙዋን እንድታቆም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመድ የሰብአዊ መብት  ኤክስፐርቶች  ኢትዮጵያ  የጸረ ሽብር ህግን  ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማፈን እና የማህበራት ነጻነትን ለመጋፋት እየተጠቀመችበት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ህጉን አላግባብ መጠቀሙዋን እንድታቆም መጠየቃቸውን-ከጄኔቫ የወጣ መግለጫ ያመለክታል። የተመድ የሰብ ዓዊ መብት ባለሙያዎች አያይሰውም ኢትዮጵያ  በተያሰው ዓመት መጀመሪያ በሰብአዊ መብት ካውንስል አባላት የጸደቀውንና በ 193 ቱም የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት እኩል ተፈጻሚ የሚሆነውን ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚፈጸሙ  ወንጀሎች ጨምሯል

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በቢቸና አውራጃ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2 የቀድሞ የቅንጅት አባሎች ተገድለዋል። ገዢው ፓርቲ እንዳደራጀ የሚነገረው ቡችሌ የተባለው ቡድን ክንዳየ አለሙና አባይነህ በተባሉ የቀድሞ የቅንጅት አባላት ላይ ስዋ ወንዝ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ግድያ መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል። ሁለቱም ሰዎች በተመሳሳይ መንገድ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድበው መሞታቸው ታውቛል። ከ10 ቀናት በፊት በሻሸመኔ ከተማ አንድ ...

Read More »

በጋምቤላ የተፈጠረው ግጭት በአኒዋ ሰርቫይቫል እይታ

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኒክ ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ አዲስ አመት ደገኞች በፈጸሙት ጥቃት 8 የመዠንገር ተወላጆች ተገድለው ፣ ከ3 ሺ በላይ የሚሆኑት መሰደዳቸውን ገልጸዋል። 835 መዠንገሮች ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠግተው በምግብ እጥረትና በብርድ ሲሰቃዩ መቆየታቸውን አቶ ኒክ ተናግረዋል። አቶ ኒክ እንደሚሉት ለግጭቱ መንስኤ የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣው የመሬት ቅርምት ፖሊሲ ነው። በዚህ ፖሊሲ የተነሳ በርካታ መዠንገሮች አካባቢውን ...

Read More »

የቋራ ህዝብ አቤቱታ

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከዚህ በላይ የት ሄደን አቤት እንደምንል ግራ ተጋብተናልም በማለት በመንግስት አሰራር ማዘናቸውንም ተናገረዋል፡፡ የቋራ ከተማ ነዋሪዎች ከወራት በፊት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት የጠየቋቸው የመልካም አስተዳደር ፣የመንገድ ፣የመብራት እና ስልክ ችግሮች ይፈታሉ በማለት አመራሮቹ ቃል ቢገቡም በዚህ አመት በተደለደለው የበጀት ቀመር ተጨማሪ በጀት ሳይያዝ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የወረዳዋ ...

Read More »

በሶማሊ ክልል ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

መስከረም ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከክልሉ ባለስልጣናት የሚደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ ወደ አዲስ አበባ እንዲሄዱ ከጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ የቀረበላቸውን ጥሪ ባለመቀበል በክልላቸው የሚገኙ ሲሆን፣ ” በኢትዮጵያ ውስጥ ከህወሃቶች በስተቀር ማንም ከስልጣን ሊያነሳኝ የሚችል ሃይል የለም” በማለት፣ የአቶ ሃይለማርያምን ጥሪ ውድቅ አድርገዋል። በምስራቅ እዝ አዛዥ ጄ/ል አብርሃም ገብረማርያም እንደሚተማመኑ የገለጹት አቶ አብዲ፣ አቶ ሃይለማርያምን ጄኔራል ...

Read More »

በሶማሊ ክልል የተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ” ገዢው ፓርቲ ለህዝብ ያለውን ንቀት ያሳያል” ተባለ

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት የህዝብ ግንኙነት ስራ አማካሪ እና የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበር በመሆን ካገለገለ በሁዋላ የተለያዩ የቪዲዮ ማስረጃዎችን በመያዝ ከአገር የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ “ኦ ኦጋዴን” በሚል ኢሳት ያስተላለፈው አጭር የዶክመንታሪ ፊልም፣ በስልጣን ላይ ያሉት ገዢዎች ለሶማሊ፣ ለኢትዮጵያና በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ያላቸውን ንቀት ያሳያል ብሎአል። ዘገባውን ከተመለከተ በሁዋላ ህመም እንደተሰማው የገለጸው አብዱላሂ፣ ...

Read More »

ኢህአዴግ ሕገመንግሥቱ የጸደቀበትን 20ኛ ዓመት ድል ባለ ዝግጅት ሊያከብር ነው

መስከረም ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህገመንግስቱ የጸደቀበትን ህዳር 29 ቀን «የብሔር ብሔረሰቦች ቀን» በሚል በየዓመቱ ሲያከብረው የቆየው ኢህአዴግ ዘንድሮ  20ኛውን ዓመት በተለየ ድምቅት በማክበር ሕዝቦች በሕገመንግስቱ የተረጋገጡላቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች አተገባበር እንከን አልባ እንደነበሩ በማጉላት በመጪው ግንቦት ወር ይካሄዳል ተብሎ በሚገመተው ምርጫ ላይ ከፍተኛ ድል ለማግኘት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ለፌዴሬሽን ምክርቤት ቅርበት ያላቸው ወገኖች ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ ባለፉት 20 ...

Read More »