ኢትዮጵያ የጸረ-ሽብር ህጉዋን፣ ሰብዓዊ መብቶችን ለማፈን መጠቀሙዋን እንድታቆም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አሳሰበ።

መስከረም ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተመድ የሰብአዊ መብት  ኤክስፐርቶች  ኢትዮጵያ  የጸረ ሽብር ህግን  ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን ለማፈን እና የማህበራት ነጻነትን ለመጋፋት

እየተጠቀመችበት እንደሆነ በመጥቀስ፤ ህጉን አላግባብ መጠቀሙዋን እንድታቆም መጠየቃቸውን-ከጄኔቫ የወጣ መግለጫ ያመለክታል።

የተመድ የሰብ ዓዊ መብት ባለሙያዎች አያይሰውም ኢትዮጵያ  በተያሰው ዓመት መጀመሪያ በሰብአዊ መብት ካውንስል አባላት የጸደቀውንና በ 193 ቱም የመንግስታቱ ድርጅት አባል ሀገራት እኩል

ተፈጻሚ የሚሆነውን ዓለማቀፍ የሰብ ዓዊ መብት አያያስ ጊሴያዊ የግምገማ ሰነድ ግምት ውስጥ እንድታስገባ መከረዋል።

ይህ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብት  ሰነድ ዓላማው ከጸረ-ሽብርተኝነት ሰመቻው ጎን ለጎን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃን ማሻሻል ጭምር እንደሆነም መግለጫው ያሳያል።

“ስጋታችንን ለመጀመሪያ ጊሴ ካሰማን ከሁለት ዓመት በሁዋላ  እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ የጸረ ሽብርተነት ህጉ ጋሴጠኞችን፣ጦማሪዎችን፣ የሰብ ዓዊ መብት ተሙዋጋቾችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ

አባሎችን ለማጥቃት እየዋለ እንደሆነ በርካታ ሪፖርቶች ደርሰውናል” ያሉት የተመድ ባለቡያዎች “ቶርቼር እና  የታሰረን ሰው ማሰቃዬት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት  ነው”ብለዋል።

“ሽብርተኝነትን መዋጋት መልካም ነው። ሆኖም በሽብርተኝነት ላይ የሚደረገው ሰመቻ  ዓለማእፍ የሰብ ዓዊመብት ጥበቃ ጥረትን ውጤታማ ማድረግ አለበት” ያሉት ኤክስፐርቶቹ፤“የ ጸረ-ሽብር ህጉ

በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ውስጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ሊካተት ያስፈልጋል።አላግባብ ሊገለገሉበት አይገባም”ብለዋል።

በኢትዮጵያ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ የመዳኘት፣ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የመደራጀት ነጻነት በጸረ ሽብር ህጉ አማካይነት በተደጋጋሚ እየተጣሰ እንደሚገኝ የተመድ ባለሙያዎች   በአጽንኦት ገልጸዋል።

“በመሆኑም የ ኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ስም ያሰራቸውን  ሰዎች እንዲፈታ ጥሪ እናቀርባለን” ያሉት የተመድ ወኪሎች፤ የታሰሩ ጋሴጠኞች፣ ጦማሪዎች፣የሰብ ዓዊ መብት ተሙዋጋቾች፣ የተቃዋሚ

ፓርቲ መሪዎችና የሀይማኖት አባቶች ያለምንም ፍራቻና መሸማቅቅ ከጠበቆቻቸው ጋር እንዲገናኙ አሣስበዋል