ጥረት ኮርፖሬት ከ 225 ሚልዩን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠመው ታወቀ

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን ንብረት በሆነው ጥረት ኮርፖሬት ውስጥ የሚገኙት ጣና ሞባይል ና ዘለቀ እርሻ ልማት ድርጅቶች በያዝነው አመት ከ225 ሚልዩን ብር በላይ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው በ2007 ዓም መግቢያ ላይ በተደረገው የድርጅቱ ግምገማ ላይ ተገልጧል። አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መሳደባቸውን ተከትሎ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አመራሮችን ለማሳመን የተደረጉ ስብሰባዎች ና የተሃድሶ መድረኮች ድርጅቱን ከፍተኛ ወጪ እንዳስወጡት ...

Read More »

በመላ ሃገሪቱ የተነደፈው  የተቀናጀ የጐልማሶች ትምህርት  ስኬታማ አይደለም ሲሉ የትምህርት  ሚኒስትሩ አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ተናገሩ፡፡

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመላ አገሪቱ ከ40 ሚሊዮን በላይ መጻፍና ማንበብ የማይችሉ ወጣት እና ጎልማሶች አሉ ያሉት አቶ ሺፈራው ፤  ይህንን የትምህርት እድል ያለገኙ ወጣቶች እና ጎልማሶች አማራጭ ትምህርት እንዲያገኙ የተደረገው ሙከራ አፈፃጸሙ ከዜሮ በታች ነው ብለዋል። በኢህአዴግ የእቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ እንደቀረበው በጎልማሶች የትምህርት አቀራረብ  አማራ 0.9፣ ኦሮምያ ፣ 0.71 ፣ደቡብ 0.63 ፣ትግራይ 2.9 በመቶ ...

Read More »

የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት የዋጋ ንረትን ማረጋጋት አልቻሉም

መስከረም ፲፬(አሥራ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዋጋ ንረትን ያረጋጋሉ ተብሎ በመንግሥት ልዩ ድጋፍ በተለይ በአዲስአበባ ከተማ የተቋቋሙት የሸማቾች የህብረት ሥራ ማህበራት በሙስናና ብልሹ አሠራር ውስጥ በመዘፈቅ አንዳንዶቹ በተቃራኒው የዋጋ ንረትን የሚያባብሱ ሥራዎች ውስጥ መሰማራታቸው መረጋገጡን ከአስተዳደሩ የተገኘ ሰነድ ጠቆመ፡፡ 250ሺ ያህል አባላት ያሉዋቸው 153 መሰረታዊ ማህበራትና 10 ዩኒየኖች እንዲሁም 1 ሺ 815 አዲስ የሸማቾችና ሌሎች ማህበራት አማካይነት የዋጋ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ለገለልተኛ የሰብአዊ መብት መርማሪዎች በሩዋን ክፍት እንድታደርግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄኔቫ ሲካሄድ በሰነበተው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ግምገማ ላይ አቋሙን ያስታወቀው አለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢትዮጵያ የሰአብአዊ መብት ድንጋጌዎችን እንደምታከብር ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን፣ በተጨባጭ ገለልተኛ ወገኖች እስር ቤቶችን እንዲገበኙ፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚካሄዱባቸውን ቦታዎች እንዲጎበኙና በደል የደረሰባቸውን ወገኖች ለማነጋገር እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል። የሰብአዊ መብት ድርጅቱ ከዚህ ቀደም እንደታዩት ...

Read More »

በባህርዳር በሚካሄደው የፖለቲካ ስልጠና ዳኞች የገዢው ፓርቲ አባል እንዲሆኑ እንደሚገደዱ ገለጹ

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመራው ስብሰባ ላይ ዳኞች የስርአቲ ደጋፊ እንዲሆኑ እየተገደዱ ባለበት ሁኔታ እንዴት ነጻ ዳኝነት ሊሰጥ ይችላል በማለት ጠይቀዋል። የድርጅት አባላት ያልሆኑ ዳኞችም ስራቸውን ለመስራት እየተቸገሩ መምጣታቸውን መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። ይሄው በመላው አገሪቱ በሚደረገው የፖለቲካ ስልጠና የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አባላት ሳይቀሩ በስርአቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ እየገለጹ ይገኛሉ።

Read More »

በደጀና አቪየሽን አንድ ወታደር  በጉልበት ስራ የምትተዳደረዋን ሴት ልጅ በጥይት ደብድቦ ገደለ

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ስራ በሚገኘው ደጀና አቬሺን ውስጥ የሚሰራ ስሙ በውል ያልታወቀ አንድ ወታደር በግቢው ውስጥ ለሚሰሩ  ሰራተኞች  በተከፈተው ሻሂ ቤት ውስጥ በአስተናጋጅነት የምትሰራዋን በደብረዘይት ነዋሪ የሆነች ወጣት በስድስት ጥይቶች ተኩሶ መግደሉን የአይን እማኞች ገለጹ። ትናንት 11 ሰአት ላይ ሰራተኞች ሰርቪስ አውቶቡስ ለመያዝ በተሰለፉበት ወቅት፣ ወታደሩ በአስራዎች እድሜ ውስጥ የምተገኘዋን ሙሉ የምትባለዋን ...

Read More »

አቶ ኦኬሎ አኳይ ተደበደቡ

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በእስር ቤት ውስጥ ከሌላ እስረኛ ጋር ተጋጭተዋል በሚል ሰበብ ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው በሁዋላ ጸሃይ ላይ ለረጅም ሰአት እንዲቀመጡ ተደርገዋል። አቶ ኦኬሎ ድብደባው የተፈጸመባቸው ቂልንጦ እየተባለ በሚጠራው  እስር ቤት ውስጥ ሲሆን፣ በእስር ቤት ሃላፊዎች መረጃ እንዲያቀርብ ተብሎ ሳይመደብ እንዳልቀረ ከሚነገርለት እስረኛ ጋር ...

Read More »

ቻይና ለአፍሪካ አገራት የማሰቃያ መሳሪያዎችን እንደምትሸጥ አምነስቲ ገለጸ

መስከረም ፲፫(አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ 130 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች ለአፍሪካ መሪዎች በእስር ቤት ጥቅም ላይ የሚሆኑ የማሰቃያ መሳሪያዎችን ይሸጣሉ። የኤልክትሪክ ንዝረት ያላቸው   ከብረት የተሰሩ ሹል ዱላዎችና ሌሎችም  የማሰቃያ መሳሪያዎች ለአፍሪካ እና ለእስያ አገራት መሸጣቸው በአህጉራቱ ውስጥ የሚታየውን ሰብአዊ መብት እረገጣ አባብሶታል። በአለም ላይ ስለት ያላቸውን የንዝረት ብረቶችን የምታመርተው ቻይና ብቻ መሆኗን የጠቀሰው አምነስቲ፣ ...

Read More »

የምእራብ አርማጭሆ ነዋሪዎች በአስተዳዳሪዎች ሽኩቻ ሰዎች እንደሚገደሉ ተናገሩ

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምዕራብ አርማጮሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ነዋሪዎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በመሬት ስሪት ፣በልማት ና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ቅሬታወች ቀርበዋል፡፡በውይይቱ ላይ በመገኘት ቅሬታቸውን ያቀረቡት ነዋሪዎቹ “የወረዳው አመራሮች እርስ በርስ በመሻኮት ስልጣን ለመያዝ ሰዎችን ያስገድላሉ የበላይ አመራሮችን የኑሮ ሁኔታ በማጥናት ቤት ሰርተዋል፣ሃብት አከማችተዋል በማለት እነርሱም የበላይ አለቆቻቸውን አይነት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ለሚያደርጉት ...

Read More »

መንግስት በግል መጽሄቶች ላይ የወሰደውን እርምጃ ሰመጉ ነቀፈ

መስከረም ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባወጣው መግለጫ ፍትህ ሚኒስቴር ሃምሌ 28፣ ቀን 2006 ዓም በፋክት፣ ሎሚ፣ ጃኖ፣ አዲስ ጉዳይ፣ እንቁ መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ያቀረበው ክስ በህገመንግስቱ የሰፈረውን ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ፣  ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው የሰብአዊ መብቶች አለማቀፍ መግለጫ አንቀጽ 19 ፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አለማቀፍ ቃልኪዳን አንቀጽ 19 እንዲሁም የአፍሪካ የሰዎችና ህዝቦች ቻርተር ...

Read More »