ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚሰጡት ደካማ አመራር ከፍተኛ ትችት ሲድርስባቸው የቆዩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ፣ ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በሁዋላ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን አቶ በላይ ፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል። ኢ/ር ግዛቸው በተመረጡ በወራት ውስጥ በርካታ የስራ አስፈጻሚ አባላት በመሪው አመራር ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን ከሃላፊነት አግለለው ቆይተዋል፡፤ በውጭ የሚኖሩ ደጋፊዎቻቸውም ቅሬታቸውን ...
Read More »የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው 10ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ በቦሌ ክፍለከተማ የሚገኝ 403 ካሬሜትር ባዶ ቦታ በ22 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ሸጠ፡፡
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደሩ የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ጽ/ቤት ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረገው የጨረታ ውጤት መሠረት በቦሌ ክፍለከተማ ለአንድ ካሬሜትር መሬት ቦታ አሸናፊ የሆነው ግለሰብ ለካሬሜትር 55ሺህ 597 ብር ከ65 ሳንቲም የሰጠ ሲሆን ግለሰቡ አሸናፊ የሆኑበት 403 ካሬሜትር ገንዘብ ሲሰላ 22 ሚሊየን 405ሺህ 852 ከ95 ሳንቲም ሆኗል፡፡ በዚሁ ክፍለከተማ ለጨረታ ከቀረቡት 38 ቦታዎች መካከል በዝቅተኛ ዋጋ ያሸነፈው ...
Read More »ሰልጣኝ ተማሪዎች በፌደራል መደብደባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ወስደው የውሎ አበል ያልተከፈላቸው የመጀመሪያ አመትና ነባር ሶስተኛ ዙር ሰልጣኞች ‹‹የውሎ አበላችን ይሰጠን›› በሚል ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው በትናንትናው ዕለት በፌደራል ፖሊስ መደብደባቸውን ተማሪዎቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ሰላማዊ ሰልፉን አደራጅታችኋል የተባሉ በርከት ያሉ ተማሪዎች መታሰራቸውንም ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ስልጠናው አርብ መስከረም 30/2007 ዓ.ም የጨረሱት ተማሪዎች መጀመሪያ ላይ እንደሚከፈላቸው ቃል ተገብቶላቸው ...
Read More »በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ በመዠንገርና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል በተነሳው ግጭት ብዙ ነዋሪዎች መገደላቸው ተሰማ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በቴፒ አካባቢ በመዠንገር ብሄረሰብና ደገኛ በሚባሉት ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ በርካታ ህዝብ ካለቀ በሁዋላ የመከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው ገብቶ ለጊዜያው ያበረደው ቢመስልም፣ ግጭቱ ወደ ጉራፈርዳ ወረዳ አቅጣጫ ተዛምቶ እስካሁን ከ20 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶችም በመሰደድ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ምንጮች እንደሚሉት ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የተነሳው ግጭት በማየሉ፣ በተለይ ...
Read More »በአዳማ በተደረገው የኢህዴድ ግምገማ አባላትና አመራሩ ተዘላለፉ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ከኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከየከተማው እና ከየወረዳው የተውጣጡ ከ300 በላይ አባላት በተሳተፉበት ግምገማ በአመራሩና በአባላት መካከል አለመግባባት ተከስቶ እርስ በርስ መዘላለፍ ደረጃ ደርሰው እንደነበር በስብሰባው የተሳተፉ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ግምገማው የተመራው በአዳማ ከተማ ከንቲባ ሲሆን፣ ከንቲባው ቀደም ብለው ያዘጋጁዋቸው አባላት በምክትሉ ከንቲባ በአቶ አህመድ የሱፍና በድርጅት ጉዳይ ሃላፊው በአቶ ፍቅሩ ጂረኛ ላይ ...
Read More »መንግስት የ20 በ80 አሰራር እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላለፈ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የ20 በ80 አሰራርን ተግባራዊ እንዲያድረጉ ታዘዋል። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ጊዜያቸውን ለመንግስት ስራ 80 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ለሚሰሩዋቸው ስራዎች እንዲያውሉ ተነግሯቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነው የሰው ጉልበት፣ ባጀት፣ ጊዜና የመሳሰሉት ነገሮች በሙሉ ለምርጫ ማደራጃ፣ ለአባላት ቅስቀሳና ማደራጃ እንዲውሉ ...
Read More »የኢህአዴግ መንግስት በኢምባሲ ውስጥ ገብተው የተቃወሙ ኢትዮጵያውያን እንዲከሰሱለት ጠየቀ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ የአሜሪካ መንግስት የአገሪቱን ሰንደቃላማ በአወረዱ ተቃዋሚዎች ላይ ክስ ይመሰርታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል። ቃል አቀባዩ ተቃዋሚዎቹ ከኤርትራ መንግስት እና ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አላቸው ብለዋል። የአሜሪካ መንግስት የኢምባሲውን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱን አለመወጣቱን የገለጡት ቃል አቀባዩ፣ ተቃዋሚዎቹን ለፍርድ ያቀርባል ብለው እየጠበቁ መሆኑንም አክለዋል። አምባሳደር ግርማ ብሩ ተቃዋሚዎቹ ክስ ...
Read More »የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች የ8 ቀን ስልጠና ቅጣት ተጣለባቸው ሲል ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠናን ለ11 ቀናት የወሰዱት የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች ስልጠናውን በደንብ አልተከታተላችሁም በሚል ተጨማሪ 8 ቀን እንዲሰለጥኑ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ሲል የዘገበው ነገረ ኢትዮጵያ፣ ከመስከረም 19/2007 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 30/2007 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና 4 ሺ 100 የከተማ አውቶቡስ ድርጅት ሰራተኞች እንዲሰለጥኑ የተደረገ ሲሆን ሰራተኞቹ ግማሹን ቀን ሰልጥነው ግማሹን ቀን እንዲሰሩ መደረጉን አስታውሷል፡፡ ...
Read More »አምባሳደር ሚኒልክ የስራ መልቀቂያ ማቅረባቸው ተሰማ
መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጄነቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ፅ/ቤት ባለሙሉ ስልጣን በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አምባሳደር ሚኒሊክ አለሙ ጌታሁን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ስራ ማግኘታቸውን ተከትሎ ሃላፈነታቸውን መልቀቃቸውን ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የደረሰን ዜና ያመለክታል። የኢህአዴግ ዋና ደጋፊ ናቸው የሚባልላቸው አምባሳደር ሚኒልክ ፣ ስርዓቱ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩ በመቆየታቸው ” ታጋይ ሚኒልክ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ...
Read More »መንግስት የባንዲራ ቀንን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ጀምሯል።
መስከረም ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ከሚፈስባቸው የመንግስት ክብረ በአላት መካከል አንዱ የሆነው የባንዲራ ቀን ዘንድሮም ጥቅምት 2 ቀን 2007 ዓም በአዲስአበባ ስታዲየም በድምቀት እንደሚከበር መንግስት አስታውቋል። “በሕዝቦች ተሳትፎና ትጋት ድህነትን ድል በመንሳት ብሔራዊ ክብሯን እና ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ ከፍ በማድረግ ላይ ያለች ሀገር!” በሚል መሪ ቃል ለ7ኛ ጊዜ በሚከበረው በዚህ በዓል ላይ ከአዲስአበባ ...
Read More »