አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በአንድ የምርት ዘመን 50 ሚሊዮን ኩንታል ልዩነት የታየበት መረጃ ሰጡ

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተቃዋሚ የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ኢትዮጵያ በምግብ ራሱዋን ችላለች በሚል  በተደጋጋሚ ቢነገርም አሁንም ስንዴ ከውጭ እያስገባን ነው በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ጠ/ሚንስትሩ “በምግብ ራሳችንን መቻላችንን” አለማቀፍ ተቋማት ሳይቀር ያረጋገጡት መሆኑን በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ በአለፈው አመት 300 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ማምረት መቻሉዋን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ የግንቦት20 በአል በሚከበርበት ወቅት ጠ/ሚኒስትሩ ባቀረቡት ንግግር ኢትዮጵያ ...

Read More »

የተወሰኑ ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት ምርጫ ቦርድ በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ ‹‹ጥያቄዎቻችን የሚመልስ አይደለም›› በሚል ሰማያዊ ፓርቲ ፣ የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ተወካዮች ረግጠው መውጣታቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ዋና ጸኃፊ ወ/ት መሊሃ ጀሃድ  ምርጫ ቦርድ እነሱ ላነሱት ጥያቄ ሌላ ጊዜ እንደሚመለስበትና በቅድሚያ ...

Read More »

በአዋሽ ወንዝ ሙላት ጉዳት የደረሰባቸው የአፋር ተወላጆች የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ነው

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአስር ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ በውሃ ሙላት ህይወቱ ለአደጋ ተጋልጦ በሚገኝበት ወቅት ከመንግስት የሚቀርብላቸው ድጋፍ አነሳ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከውሃ ሙላቱ የተረፍነዎች በምግብ እጦት እየተሰቃየን በመሆኑ መንግስት በአፋጣኝ ይደረስልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል። አፋጣኝ መልስ ካልተሰጠም እስካሁን ከታየው በላይ አስከፊ የሆነ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ተፈናቃዮች አስጠንቅቀዋል። ከአፋር ህዝብ እንደተወከሉ የሚገልጹ የአገር ሽማግሌዎች በጎርፉ ከ87 ...

Read More »

በዳርፉር ሶስት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገደሉ

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ዳርፉር ኮርማ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የውሃ ጉድጓድ ሲጠብቁ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 2ቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ አንደኛው በጽኑ ቆስሎ የነበረ ቢሆንም፣ ትንሽ ቆይቶ ህይወቱ አልፎአል። ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች እነማን እንደሆኑ በውል አልታወቁም።   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ግድያውን በጽኑ አውግዘው፣ ግድያውን የፈጸሙት አካላት አለማቀፍ ህግን መጣሳቸውን ማወቅ አለባቸው ብለዋል።

Read More »

ኢትዮጵያ ሃኪሞቿንና ሰራዊቷን ወደ ምእራብ አፍሪካ ለመላክ መወሰኑዋ አነጋጋሪ ሆኗል

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ አፍሪካዊያን ወንድሞቻችንን እህቶቻችን ለመርዳት ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጽያዊን የህክምና ባለሙያዎችን ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎችም ተቋማት በሸታው ወደተስፋፋባቸው የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ለመላክ መወሰኑን አረጋግጠዋል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ እንዳሉት «ኢትዮጽያ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛዋ ሀገር እንደመሆንዋ መጠን አፍሪካዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ለማገዝ የራሳችን ድርሻ መወጣት አለብን የሚል አቋም ተይዟል፡፡ መከላከያ ሠራዊት ውስጥ ያሉና ሌሎችም የጤና ሙያተኞች በፈቃደኝነት ...

Read More »

በአፋር ክልል በአዋሽ ወንዝ ሙላት ከ87 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ500 በላይ ሰዎች ደብዛቸው መጥፋቱን ኗሪዎች ለአለም ቀይመሰቀ ልድርጅት አመለከቱ

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለድርጅቱ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለኢሳት እንደገለጹት የኢትዩጵ ያመንግስት ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰባቸውም በማለት እያቀረበ ያለውን ሪፖርት ነዋሪዎቹ አጥብቀው ተቃውመዋል። 87 ሰዎችን በእጃን  ቀብረናል ያሉት ኗሪዎች ዜናው የተነገረው ጉዳት ከደረሰ ከሳምንት በኃላ ሲሆን እርዳታ የመጣውም ብዙ ነገረ ከወደመ ከስድስት ቀናት በሁዋል መሆኑ ችግሩን የከፋ አደርጎታል ሲሉ አመልክተዋል። በድርጊቱ እጅግ ማዘናቸውን የገለጹት ነዋሪዎች ተቆርቋሪ መንግስት ...

Read More »

በተቃዋሚዎች የሚረጨውን መርዝ ለማርከስ ለዩኒቨርስቲ ምሁራንን ለሌሎች ዜጎች የውይይት መድረኮች መዘጋጀታቸውን አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-99 በመቶ በላይ የኢህአዴግ አባላት በሞሉበት ፓርላማ ውስጥ ብቸኛ የሆኑት የአንድነት ፓርቲ ተመራጩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ በቅርቡ መንግስት ለዩኒቨርስቲ  መምህራን፣ ተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች የሚሰጠውን የፖለቲካ ስልጠና አስመልክቶ ላቀረቡት ጥያቄ መልስ የሰጡት ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ ውይይቱን ማድረግ ያስፈለገው ትምክህተኞች፣ ጸረ ሰላም ሃይሎችና ጠባቦች የሚረጩት መርዝ ትክክል አለመሆኑን ለማሳየት ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ባለስልጣናትና ...

Read More »

በጋምቤላ ያለው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች  አቦቦ በሚባለው አካባቢ የተጀመረውን ግጭት ተከትሎ ወታደሮች የሚወስዱትን እርምጃ በመቃወም መንግስት ያስታጠቃቸው ከ15 በላይ ታጣቂዎች ስርአቱን አናገለግልም በማለት መጥፋታቸውንና የመከላከያ ሰራዊት አባላትም ታጣቂዎችን ለመያዝ አሰሳ መጀመራቸውን ገልጸዋል። የመንግስት ታጣቂዎች የነበሩ የጋምቤላ ተወላጆች ከመጥፋታቸው በፊት በመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በመወሰዱት እርምጃ ከ2 ያላነሱ የመከላከያ አባላት መገደላቸውና የተወሰኑትም መቁሰላቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በመዠንገር አካባቢ ...

Read More »

12 ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ አስገቡ

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲዎቹ በደብዳቤያቸው ከዚህ ቀደም ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸውና ሁኔታዎች ከቁጥጥር ውጭ እንዳይወጡ በመስጋታቸው ደብዳቤ ለመጻፍ መገደዳቸውን ገልጸዋል። ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው “የፖለቲካ አመራሮችን ማስፈራራት፣ የአካላዊ ጉዳት ማድረስ፣ በሃሰት ውንጀላና የፈጠራ ክስ ማሰር እየተጠናከረ መምጣት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከህዝብ ጋር እንዳይገናኙና አላማቸውን ፣ፕሮግራማቸውንና አማራጭ ፖሊሲዎቻቸውን ለህዝብ እንዳያቀርቡ ማድረግ፣ ገዢው ፓርቲ መንግስታዊ መዋቅርን በመጠቀም የምርጫ ቅስቀሳ እየዳረገ መሆኑን፣ ...

Read More »

በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥቅምት ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኖርዌይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ በተጠራ ጉባኤ ላይ የተገኙትን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በመቃወም የተጠራው ሰልፍ የአገሪቱን ዋነኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ኢነርኬን ሽፋን አግኝቷል። ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በተጠራው ተቃውሞ፣ ኢትዮጵያውያን የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ኖርዌይ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽመው መንግስት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት እንድታቆም ጠይቀዋል።በኢትዮጵያ ለሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት ኖርዌይ ተጠያቂ ...

Read More »