በዳርፉር ሶስት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ተገደሉ

ጥቅምት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ዳርፉር ኮርማ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የውሃ ጉድጓድ ሲጠብቁ ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 2ቱ ወዲያውኑ ሲገደሉ አንደኛው በጽኑ ቆስሎ የነበረ ቢሆንም፣ ትንሽ ቆይቶ ህይወቱ አልፎአል።

ጥቃቱን የፈጸሙት ታጣቂዎች እነማን እንደሆኑ በውል አልታወቁም።   የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ግድያውን በጽኑ አውግዘው፣ ግድያውን የፈጸሙት አካላት አለማቀፍ ህግን መጣሳቸውን ማወቅ አለባቸው ብለዋል።