በኢትዮጵያ ፖሊዮ አሁንም ህዝቡን እያጠቃ ነው ሲል ዩኒሴፍ አስታወቀ

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2013 በነበረው ጊዜ ከፖሊዮ ነጻ አገር ተብላ የተወደሰች ቢሆንም፣ ካለፉት 2 አመታት ጀምሮ በሽታው እንደገና መታየቱን ዩኒሴፍ አስታውቋል። ባለፈው አመት 10 የፖሊዮ ተጠቂዎች መታየታቸውን የገለጸው ዩኒሴፍ፣ የበሽታው እንደገና መከሰት ለአገሪቱ ፣ ለቤተሰቦችና ለህጻናቱ እጅግ አደገኛ ክስተት ነው ብሎአል። ኢትዮጵያ በሽታውን ለመከላከል ተጨማሪ 2 ሚሊዮን ዶላር እንደሚሰጣት ዩኒሴፍ ...

Read More »

ከ50 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊጓዙ ሲሉ መያዛቸውን የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ

ጥቅምት ፲፫(አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ መንገድ መግባታቸውን የገለጸው የኬንያ ፖሊስ፣  54ቱ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቤት ውስጥ ታጭቀው ተገኝተዋል ብሎአል። ሰዎቹን ወደ ኬንያ ያመታው ግለሰብ መጥፋቱንም ፖሊስ ገልጿል። ኢትዮጵያውያንን ወደ ደቡብ አፍሪካ ማሻገር ትልቁ የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ፖሊስ ገልጿል። ወደ ደቡብ አፍሪካ እንጓዛለን በማለት ሙከራ ያደረጉ ኢትዮጵያውያን፣ በ ዝምባብዌ፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያና በሌሎችም አገራት ታስረው እንደሚገኙ ዘገባዎች ...

Read More »

በአዲስ አበባ ውስጥ የሚታየውን የሃይል እጥረት ለመቅርፍ ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ባለሙያዎች ገለጹ

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንደይጠቀስ የፈለጉ በኢትዮጵያ መብራት ሃይል ስር የሚሰሩ ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት በአዲስ አበባ የሚታየው የመብራት ሃይል መቆራረጥና መጥፋት ነዋሪውን ለስቃይ እየዳረገው ነው። እናቶች የአቦኩትን ሊጥ ለመጋገር ሲዘጋጁ መብራት ይጠፋና ሊጡ የሚደፋበት ጊዜ መኖሩን የሚናገሩት ሰራተኞች፣ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ለመስሪያ ቤቱ በማቅርብ መልስ ሲያጡ የመብራት ሃይል ሰራተኞች ለጥገና ሲንቀሳቀሱ መኪኖቻቸውና ሰራተኞች  በተበሳጩ ሰዎች እንደሚመቱ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት በወንጀልና በሽብር የሚጠረጥራቸውን ሰዎች በሱዳን ግዛት ውስጥ በቀላሉ ለመያዝና ንብረቶቻቸውን ለመውረስ የሚያስችለው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ፡፡

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረቂቅ አዋጁ ሁለቱ ሀገራት በወንጀል የጠረጠሩትን ዜጎች በመያዝ ለፈላጊው ሀገር አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችላቸው ነው፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተመለከተው በዚህ ትብብር መሰረት መረጃው በሚፈለገው ሀገር አግባብነት ባለው ተቋም ህጋዊ መጠየቂያ ደብዳቤ መሰረት ለተጠያቂው ሀገር በመላክ ይከናወናል ይላል፡፡ ስምምነቱ በተጠርጣሪ ወንጀለኞች ጉዳይ ማስረጃዎችን የመሰብሰብ፣ ቃል የመቀበል፣ የሚያዙ ሰዎችን ወይንም ምስክሮች ለትብብር ጠያቂው ሀገር የፍርድ ...

Read More »

በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት ላይ እተከሰተ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የቤተ ክርስቲያኗ አመራሮች አስታወቁ፡፡

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅዱስ ላሊበላ ገዳም የሰው ሃይል አስተዳደር የሆኑት ቀኝ ጌታ በላይ አናውጥ ከልዩ ልዩ አካባቢ ለመጡ ጋዜጠኞችና ጎብኝዎች እንደ ገለጹት ገዳሙ በዝናብና ጸሃይ እየደረሰበት ያለው ጉዳት ቅርሶቹን በአስከፊ ደረጃ እያፈረሳቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቅርሶቹን ከጸሐይና ዝናብ ይከላከላል ተብሎ ከለጋሽ ሃገሮች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው መጠለያም ምሰሶዎች ብረት የተተከሉት በቤተ መቅደሶቹ ላይ በመሆኑና የብረቱም ክብደት ...

Read More »

በኦሮሚያ ና በአማራ ከልሎች የግሪሳ ወፍ መከሰቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ጥቅምት ፲፪(አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግሪሳ ወፍ በሰብል ላይ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ዛሬ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት በፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ከበደ ላቀው እንዳሉት በኦሮሚያ ክልል ዝዋይና መቄ አካባቢዎች 8 ሚሊዮን ሚጠጋ የግሪሳ ወፍ ተከስቷል፡፡ በአማራ ክልልም ሰሜን ሸዋ ቀወት እንዲሁም ...

Read More »

የፌደራል ኦዲተር ባለፉት ሶስት አመታት እርምጃ ያልተወሰደባቸውን መስሪያ ቤቶችን ስም ለተወካዮች ምክር ቤት አቀረበ

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት የመንግስት ሃብትና ንብረትን ላለፉት ሶስት አመታት የህዝብን ሃብት በህገወጥ መንገድ በማባከን ሪኮርድ የሰበሩ መንግስታዊ ተቋማት እርምጃ እንዳልተወሰደባቸው ለተወካዮች ምክር ቤት ያዘጋጀው ሪፖርት ያመለክታል። የተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ግምገማው ለኢትዮጵያ ህዝብ መቅረብ የለበትም ብለዋል። ባለፉት 3 አመታት ሂሳባቸውን በወቅቱ ያልዘጉ መ/ቤቶች የፋይናንስና ኮሚኒኬሽን መ/ቤቶች ፣ የግዢ ...

Read More »

በአፋር የፌደራል ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው ሌላ ሰው አቆሰሉ

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአሚባራ በአፋርና በኢሳ መካከል የተነሳውን ግጭት  ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው ገድለው ሌላ የአፋር ተወላጅን ደግሞ አቁስለዋል። በአካባቢው ውጥረቱ አሁንም መቀጠሉን ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ከትናንት ጀምሮ ገዋኔና ቡድመዳ ወረዳዎች በጎርፍ መጥለቅለቃቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት በቂ ድጋፍ እያደረገ አይደለም በማለት ወቅሰዋል።  በአዋሽ ቀበና ላይ ...

Read More »

የህዝብ ግንኙነት ካድሬዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ሊዘምቱ ነው

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አሰልጥኖ በፌዴራል የመንግስት ተቋማት በህዝብ ግንኙነት ኃላፊነት ለመደባቸው ካድሬዎች የሁለት ቀናት የማህበራዊ ድረገጾች አጠቃቀም ስልጠና በመስጠት በተለይ በግንቦት ወር ከሚካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ እንዲሳካ የበኩላቸውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለጸው የኮምኒኬሽን ጽ/ቤቱ በሚኒስትሮች ምክርቤት ደንብ ቁጥር 158/2001 ሲቋቋም በመንግስትና ...

Read More »

የኢህአዴግ አመራሮች ቀደም ብለው የነበሩትን መንግስታት በማንኳሰስ የራሳቸውን ስራ ማሞገስ በየመድረኩ ተጠናክሮ መቀጠሉ አግባብ እንዳልሆነ ተነገረ፡፡

ጥቅምት ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በአዳማ ከተማ   ለጋዜጠኞች ባዘጋጀው ሴሚናር ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ተወክለው በስብሰባው በመገኘት ንግግር ያደረጉት አቶ ናስር ለገሰ ባቀረቡት የኢትዮጵያ ሰፖርት ታሪክ ንግግራቸው የቀደሙት መንግስታትን ስራ በማጣጣል የገዢውን መንግስት ስራ በማግዘፍ ባቀረቡት ጽሁፍ ከጋዜጠኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ የገዢው መንግስት አሁን የሚያንቀሳቅሰው ከፍተኛ በጀት ስፖርቱ እንዲጎለብት ለማድረግ ከልብ ከመጣር ይልቅ ስፖርቱን ለፖለቲካ ...

Read More »