አንድነት ፓርቲ አቶ በላይ በፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾመ

ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚሰጡት ደካማ አመራር ከፍተኛ ትችት ሲድርስባቸው የቆዩት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው ፣  ስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ካሳወቁ በሁዋላ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩትን

አቶ በላይ ፈቃዱን ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል።

ኢ/ር ግዛቸው በተመረጡ በወራት ውስጥ በርካታ የስራ አስፈጻሚ አባላት በመሪው አመራር ደስተኛ ባለመሆን ራሳቸውን ከሃላፊነት አግለለው ቆይተዋል፡፤ በውጭ የሚኖሩ ደጋፊዎቻቸውም ቅሬታቸውን በተለያዩ መንገዶች ሲገልጹ ቆይተዋል።

ስብሰባው በሙሉ መግባባት የተካሄ እንደነበር ተሳታፊዎች ገልጸዋል።