መንግስት የ20 በ80 አሰራር እንዲጀመር ትእዛዝ አስተላለፈ

መስከረም ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተከትሎ የኢህአዴግ አባላት የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች የ20 በ80 አሰራርን ተግባራዊ እንዲያድረጉ ታዘዋል። የኢሳት የኢህአዴግ ምንጮች እንደገለጹት የመንግስት ሰራተኞች 20 በመቶ ጊዜያቸውን ለመንግስት ስራ 80 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ ከምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ለሚሰሩዋቸው ስራዎች እንዲያውሉ ተነግሯቸዋል። 80 በመቶ የሚሆነው የሰው ጉልበት፣ ባጀት፣ ጊዜና የመሳሰሉት ነገሮች በሙሉ ለምርጫ ማደራጃ፣ ለአባላት ቅስቀሳና ማደራጃ እንዲውሉ ትእዛዝ መተላለፉን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

የኢህአዴግ ባለስልጣናት መጪውን ምርጫ አስታከው በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየዞሩ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ናቸው።