ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዜጎቹ ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ አልሸባብ በቦሌ አካባቢ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው ገልጿል። ኤምባሲው አዲስ መግለጫ እስከሚወጣ ድረስ ዜጎቹ ከሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የማምለኪያ ቦታዎች፣ ከገበያ ቦታዎችና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲርቁ መክሯል። ጥቃቱ የሚፈጸምበት ትክክለኛ ቦታ ባይታወቅም ፣ የአሜሪካ ዜጎች የራሳቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ አሳስቧል። የኢትዮጵያ ...
Read More »ጸሃፊዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው
ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩት ጸሃፊዎች እና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል። የተከሳሽ ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቢ ህግ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ መልስ ለመስጠት ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ይዟል። ተከሳሾቹ ነጭ ልብስ ለብሰው መቅረባቸውን፣ በጥሩ መንፈስና ጥንካሬ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል። መንግስት ስርአቱን ይተቻሉ የሚላቸውን ...
Read More »ማህበረ ቅዱሳን ለሚካሄድበት የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠየቀ
ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው ማህበሩ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለሁሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ ማህበሩ” በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት በተጠሩ ስብሰባዎች የተፈጸምበት የስም ማጥፋት ...
Read More »በደቡብና ጋምቤላ ድንበር አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ሌሎችም የጋምቤላ አካባቢዎች እየተስፋፋ ነው
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ50 በላይ የመንግስት ፖሊሶች፣ ወታደሮችና ታጣቂዎች የተገደሉበት የደቡብ እና ጋምቤላ ድንበሮች አዋሳኝ በሆነው ጉራፈርዳ ወረዳ አካባቢ የተጀመረው ግጭት ወደ ጋምቤላ ከተማና አቦቦ ወረዳ መዛመቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ትናንት ምሽት በጋምቤላ ከተማ በተነሳ ግጭት ከ3 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ዛሬ ከተማዋ በመከላከያና ፖሊሶች ተወራለች። የመንግስት ስራና ትምህርትቤቶች ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን፣ በአብዛኛው አካባቢዎች ከቦታ ...
Read More »በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ በርካታ ዜጎች ጉዳት ደረሰባቸው
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የተነሳ የአዋሽ ወንዝ በመሙላቱ በአሚባራና ዱላሳ ወረዳዎች ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎች እንደሚሉት በአሚባራ አካባቢ ከ5 ሺ ሄክታር በላይ የታረሰ መሬት መውደሙን፣ የ7 ቀበሌ ሰዎች በውሃ መከበባቸውንና ንብረታቸው በውሃ መወሰዱን እንዲሁም አንድ የእርሻ ምርምር ማእከል በውሃ መወሰዱን ገልጸዋል። እስካሁን የሞቱ ሰዎች መኖራቸውን ለማወቅ በአይቻልም፣ አንዳንድ ...
Read More »የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ችሎት ቢጀምርም የችሎት መጓተት እየተፈታተነው ነው ሲል ድምጻን ይሰማ ገለጸ
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት የችሎት መቋረጥ በሁዋላ ስራ የጀመረው ፍርድ ቤቱ፣ አንድ ምስክር እንካ በአግባቡ ሳያዳምጥ መብራት ሄደ በሚል ምክንያት እንዲቋረጥ መደረጉን ገልጿል። ሰኞ በነበረው ችሎት አቶ አህመድ ኡመር የተባሉ ምስክር እየተናገሩ ባለበት ጊዜ ምስክርነታቸው ሳይጠናቀቅ መብራት በመሄዱ ለማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ቢሰጥም ዛሬ ማክሰኞ በተመሳሳይ ሁኔታ ችሎቱ ሳይካሄድ መቅረቱን ድምጻችን ይሰማ ገልጿል፡፡ ለዛሬው ችሎት መቆረጥ የቀረበው ...
Read More »እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከፍተኛ ቅጣት ሊጠብቀው ይችላል
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለማፍረስ ” በሚል ወንጀል የተከሰሰው እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ከተባለ በሁዋላ፣ ውሳኔውን በእስር ላይ ሆኖ እንዲሰማ ፍርድ ቤት ባዘዘው መሰረት ወደ እስር ቤት ተልኳል። ጋዜጠኛ ተመስገን የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በመሆን ሲሰራ ” ድህረ ምርጫ 1997 ዓምን ተከትሎ ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ በተደረገው የአደባባይ አመጽ እንዲሁም ...
Read More »ስድስት ወታደራዊ መኮንንኖች ተሾሙ
ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ3 ወታደራዊ አዛዦች የሌተናል ጄኔራል ማእረግ ሲሰጥ ለቀሪዎቹ ደግሞ የሜጀር ጄኔራል መእረግ ሰጥቷል። ማእረጉ ከተሰጣቸው ጄኔራሎች ውስጥ 4ቱ የትግራይ አንዱ የአማራና አንዱ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኮንኖቹ ባስመዘገቡት ውጤት ማእረግ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል። ግንቦት7 ከአራት አመት በፊት ያወጣውን የወታደራዊ መኮንኖች የብሄር ተዋጽኦ ጥናት ክለሳ መሰረት አድርጎ ይፋ ባደረገው መረጃ ከ10ሩ ...
Read More »በሸኮ መዠንገር ታጣቂዎችና በፌደራል ፖሊሶች መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ ከ50 በላይ የፌደራልና የመከላከያ አባላት ተገደሉ።
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የፌደራል ፖሊሶችን ልዩ ሃይልንና መከላከያን ባቀፈው የመንግስት ጦርና፣ መሳሪያ በታጠቁ የብሄረሰቡ ተወላጆች መካከል በተደረገው ውጊያ ከ40 በላይ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ከ10 ያላነሱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ 4 ታጣቂ ሚሊሺያዎችና 3 የወረዳ ፖሊሶች ተገድለዋል። የሟቾቹ አስከሬን በሚዛን አማን ሆስፒታል እንዲገባ ከተደረገ በሁዋላ፣ ዘመድ ያላቸው ወደ ዘመዶቻቸው ሲሸኙ፣ የቀሪዎቹ የቀብር ...
Read More »ኢህአዴግ አመራሮች በሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት እንደተከፋፈሉ ነው
ጥቅምት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊ ክልል በፕሬዚዳንቱና በ7 የስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል ተፈጥሮ የቆየውን ውዝግብ ለመፍታት ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሁሉንም ወገኖች አዲስ አበባ ቢጋብዙም፣ ፕሬዚዳንቱ አቶ አብዲ ሙሃመድ የጠ/ሚሩን ጥሪ ውድቅ በማድረግ የራሳቸውን ጉባኤ በመጥራት አዲስ የስራ አስፈጻሚዎችን ሾመዋል። ባለፈው መስከረም 24 ቀን በፊቅ ከተማ በተደረገው ጉባኤ፣ ፕሬዚዳንቱ የራሳቸውን ደጋፊዎችና ዘመዶቻቸውን በስራ አስፈጻሚነት አስመርጠዋል። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ...
Read More »