ስድስት ወታደራዊ መኮንንኖች ተሾሙ

ጥቅምት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ለ3 ወታደራዊ አዛዦች የሌተናል ጄኔራል ማእረግ ሲሰጥ ለቀሪዎቹ ደግሞ የሜጀር ጄኔራል መእረግ ሰጥቷል።

ማእረጉ ከተሰጣቸው ጄኔራሎች ውስጥ 4ቱ የትግራይ አንዱ የአማራና አንዱ የኦሮሞ ተወላጅ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መኮንኖቹ ባስመዘገቡት ውጤት ማእረግ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

ግንቦት7 ከአራት አመት በፊት ያወጣውን የወታደራዊ መኮንኖች የብሄር ተዋጽኦ ጥናት ክለሳ መሰረት አድርጎ ይፋ ባደረገው መረጃ ከ10ሩ ወታደራዊ እዝና ቁጥጥር ዘርፎች የበላይ ሃላፊዎች ውስጥ 7ቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸው።