ጸሃፊዎች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ጥቅምት ፭(አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩት ጸሃፊዎች እና ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፍርድ ቤት ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት አሰናብቷቸዋል።

የተከሳሽ ጠበቆች ላቀረቡት የክስ መቃወሚያ አቃቢ ህግ ምላሽ የሰጠ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ መልስ ለመስጠት ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ይዟል።

ተከሳሾቹ  ነጭ ልብስ ለብሰው መቅረባቸውን፣ በጥሩ መንፈስና ጥንካሬ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ዘጋቢያችን ገልጿል። መንግስት ስርአቱን ይተቻሉ የሚላቸውን ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎች በማሰር የውስጥ ችግሩን ለመፍታት ይሞክራል በሚል ተደጋጋሚ ትችት እየደረሰበት ነው።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ካውንስል መንግስት በጸረ ሽብር ትግል ስም የሚያስራቸውን የህሊና እስረኞች እንዲፈታ ወይም ፍትሃዊና አፋጣኝ መልስ እንዲሰጥ መጠየቁ ይታወቃል።