(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2011)የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አስክሬን ሽኝት ተደረገ። ህይወታቸው ባለፈበት ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ዛሬ በተካሄደ የሽኝት ፕሮግራም ከተለያዩ የጀርመን ከተሞችና ከሌሎች ሀገራት የመጡ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች መገኘታቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል ። በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በተዘጋጀው የስንብትና የሽኝት ፕሮግራም የዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቅርብ ጓደኞችና አብሮ አደጎች ምስክርነቶችን ሰተዋል። በሃይማኖታዊ ዝማሬና ጸሎት ሽኝቱ የተከናወነ ...
Read More »የጎሳ ፖለቲካ በህግ ይታገድ የሚለው ዘመቻ አስተባባሪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ላኩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2011)የጎሳ ፖለቲካ በህግ ይታገድ በሚል ዘመቻ በማድረግ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ግብረሃይሎች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያዘጋጁትን ደብዳቤ አስገቡ። ግብረሃይሎቹ በአሜሪካን የኢትዮጵያ አምባሳደር በኩል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤውን መላካቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ግብረሃይሎች ከአምባሳደር ፍጹም አረጋ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውም ታውቋል። ደብዳቤውን ለአምባሳደሩ ካስገቡት መካከል የኢትዮ-አሜሪካ ሲቪል ካውንስል ፕሬዝዳንት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ይህን ...
Read More »አዴፖ ህገመንግስቱና ፌደራሊዝሙ እንዲሻሻል መጠየቁን አስታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2011)ህገመንግስቱና ፌደራሊዝሙ እንዲሻሻል አዴፖ መጠየቁን የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ገለጹ። በፋኖ ስም በየመንገዱ መሳሪያ መያዝና ህገወጥ ስራ መስራት አይቻልም ሲሉም አሳስበዋል። ፕሬዝዳንቱ ዶክተር አምባቸው መኮንን ዛሬ ጎንደር ላይ በተዘጋጀ ህዝባዊ ስብስባ ላይ እንደገለጹት ህገመንግስቱንና ፌደራሊዝሙን ማሻሻልን በተመለከተ ቀድሞ ጥያቄ ያቀረበው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ ነው። ዶክተር አምባቸው በፋኖ ስም የሚደረገው ህገወጥ ተግባርን በማውገዝ በዚህ ድርጊት ላይ የተሰማሩትን ሃይሎች ከድርጊታቸው ...
Read More »የዜጎችን ህይወት ያጠፉ፤ የአካል ጉዳት ያደረሱና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2011) በሃገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የዜጎችን ህይወት ያጠፉ፤ የአካል ጉዳት ያደረሱና ንብረት ያወደሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ መንግስት ርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዜጎች ላይ የህይወትና የንብረት ጉዳት ያደረሱት አካላት ላይ የሚወሰደው ርምጃ ፈጣን እንዲሆን በዛሬው ዕለት አሳስቧል፡፡ መንግስት በበኩሉ ህዝብ ላይ ጉዳት ያደረሱ ከ600 በላይ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማድረጉን አስታውቋል፡፡ በተያያዘ ዜና በኢትዮጵያ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ...
Read More »በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር ዋለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 25/2011) በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ። በንጹሃን ላይ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የአማራና የቤንሻጉል ጉምዝ ክልሎች አስታውቀዋል። የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ ለኢሳት እንደገለጹት በጃዊ ወረዳ ሶስት ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉ ሰላማዊ ዜጎች ቁጥርና የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት ለማወቅ ምርመራ በመካሄድ ላይ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በጃዊ ...
Read More »የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነስርዓታቸው የፊታችን ዕሁድ ይፈጸማል
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)ባለፈው ቅዳሜ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የፊታችን ዕሁድ የቀብር ስነስርዓታቸው እንደሚፈጸም ተገለጸ። አስክሬናቸው ቅዳሜ ሚያዚያ 26 ከጀርመን ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባም መንግስት አስታውቋል። በብሔራዊ ደረጃ የሚፈጸመው የቀብር ስነስርዓት ኮሚቴ ተቋቁሞ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑም ታውቋል። በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ በዶክተር ኢዮብ ተካልኝና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የሚመራው የቀብር ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ ተሸላሚ ሆኑ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2011)ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የ2019 የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት ተሸላሚ ሆኑ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአፍሪካ ቀንድ በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደረስ ባደረጉት አስተዋጽኦ ለሽልማት መብቃታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የትምህርት፣የሳይንስና የባህል ተቋም ዩኔስኮ ይፋ አድርጓል። በቀድሞ የአይቬሪኮስት ፕሬዝዳንት ፌሊኒክስ ሃፌፍ- ቦኒይ ስም የሚጠራውን የዩኔስኮ የሰላም ሽልማት የተቀዳጁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በሀገር ውስጥ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ለመውሰድ በጀመሩት ጥረትም አድናቆትን እንዳገኙ ...
Read More »የኢትዮጵያ የእስልምና ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱ መድረሱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የትላንቱ ጉባዔ የኢትዮጵያ የእስልምና ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው ሲል አስታወቀ። በትላንቱ ጉባዔ ድል ኮሚቴው ምስጋናውን ለመላ የኢትዮጵያ ህዝብ አቅርቧል። የኮሚቴው አባል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ለኢሳት እንደገለጹት የኢትዮጵያ ሙስሊም ለዓመታት ሲጠይቅ የነበረውን በአግባቡ ምላሽ ያገኘበት ጉባዔ ሆኖ ተጠናቋል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም ከአዲሱ የዑለማ ምክር ቤትና ቦርድ ጋር ተባብረው ...
Read More »በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲቆም ለመጠየቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 24/2011) በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት እንዲቆም ለመጠየቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተደረገ በተለያዩ ከተሞች የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተጠናቋል፡፡ የሰልፉ ትኩረት በተለያዩ አካባቢዎች ያለው የአማራ መፈናቀል እና ሞት ይቁም የሚል ነው ተብሏል። የአማራ ክልል ርእሰ ከተማ ባህር ዳር ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ መነሻውን በተለምዶ ገበያ አካባቢ በማድረግ መድረሻውን ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ...
Read More »ልጃቸውን የገደለባቸው ተጠርጣሪ ለአሜሪካ ተላልፎ በመሰጠቱ እፎይታን ማግኘታቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)ልጃቸውን የገደለባቸው ተጠርጣሪ ለአሜሪካን ተላልፎ በመሰጠቱ እፎይታን ማግኘታቸውን ኢትዮጵያዊው ወላጅ አባት ገለጹ። ከሁለት ዓመት በፊት በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ሁለት ኢትዮጵያውያን በመግደል ወደ ኢትዮጵያ ሸሽቶ የነበረው ተጠርጣሪን ኢትዮጵያ አሳልፋ መስጠቷ በልጃችን ሞት የተሰበረውን ልባችንን የሚክስ ነው ሲል ወላጅ አባት አቶ ግርማ ዮሃንስ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል። እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በህዳር 2016 በአሜሪካ ቨርጂኒያ ስፕሪንግ ፊልድ በተባለ ከተማ ነዋሪ ...
Read More »