(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በማንነቴ በደረሰብኝ ጥቃት አየር መንገዱን ለቅቄ ወደ ግብርና ገብቼአለሁ በሚል በአማራ ቴሌቪዥን ለተናገሩት ግለሰብ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምላሽ ሰጠ። በዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ተወለደ ገብረማርያም ፊርማ በተሰጠ ምላሽ የአማራ ቴሌቪዥን አየር መንገዱን ይቅርታ እንዲጠይቅም ያሳስባል። ከባርነት ነጻነት ሞትን እመርጣለሁ በሚል ርዕስ በአማራ ቴሌቪዥን በቀረበው ዘገባ ካፒቴን ዮሀንስ ተስፋዬ በማንነቱ የሚደርስበት በደልና ስቃይ ከፍተኛ በመሆኑ መቀጠል ባለመቻል ስራውን መልቀቁን ...
Read More »የጋምቤላ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በጋምቤላ እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመቃወምና የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን የለውጥ እንቅስቃሴ የሚያደናቅፉ አመራሮች ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነገ በሚኒሶታ ተጠራ። የጋምቤላን ሁኔታ መንግስት ትኩረት እንዲሰጠው ጫና ለመፍጠር ታስቦ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በሚኒሶታና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲገኙ ጥሪ ተደርጓል። በነገው ዕለት በሴን ፖል የሚኒሶታ ግዛት ምክር ቤት ህንጻ የሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በጋምቤላ እየተካሄደ ያለው እስርና ...
Read More »የቡራዩ ነዋሪዎች እስካሁን ስራ አለመጀመራቸው ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በቡራዩ ከተማ ተፈጥሮ በነበረው ብጥብጥ ሆቴሎቻቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የከተማው ነዋሪዎች እስካሁን ስራ ያለመጀመራቸውን አመለከቱ፡፡ ባለሆቴሎቹ ለኢሳት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለደረሰው የንብረት ውድመት የከተማው መስተዳድር የወደመውን ንብረት ምዝገባ እና ግምት ቢያካሂድም እስካሁን ወደስራ እንዲመለሱ ለማድረግ ይህ ነው የሚባል ተግባር አላከናወነም፡፡ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ በበኩላቸው የወደመውን ንብረት የመመዝገቡ ስራ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡ ለተፈናቃዮቹ ማቋቋሚያም ሆነ ...
Read More »ሼህ ወርቁ ኑሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011)በደቡብ አፍሪካ ለኢትዮጵያ ነጻነትና ፍትህ ድምጻቸውን በማሰማት የሚታወቁት ሼህ ወርቁ ኑሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ሼህ ኑሩ ላለፉት 20 ዓመታት በደቡብ አፍሪካ በሚካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችና ህዝባዊ ስብሰባዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል አንስቶ በዋና ዋና የፖለቲካ ንቅናቄዎች ውስጥ ሚናቸው በጉልህ የሚጠቀሰው ሼህ ኑሩ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የነጻነት አርማ ተደርገው እንደሚታዩም ...
Read More »የቤንሻንጉል ተፈናቃይ እናቶች በመጠለያ ውስጥ ልጆቻቸውን ተገላገሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው በኦሮሚያ ክልል ከተጠለሉ ተፈናቃዮች ውስጥ ከ20 በላይ ነፍሰ ጡር እናቶች በመጠለያ ውስጥ መገላገላቸው ታወቀ። ሌሎች 53 ወራቸው የገባ ነፍሰ ጡሮች የመውለጃ ጊዜያቸውን እየጠበቁ መሆናቸው ተመልክቷል። የነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ነፍሰ ጡሮችንና እመጫቶቹን በመንከባከብ ላይ መሆኑን መረጃው አመልክቷል። የቤንሻንጉል ክልል ካማሼ ዞን ባለስልጣናት ከስብሰባ ሲመለሱ ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ በካማሼ ዞን ሰላማዊ ነዋሪዎች ...
Read More »በሸካ ዞን ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በሸካ ዞን ቴፒ በየኪ ወረዳ እርምጭ ቀበሌ ጎረፌ በሚባል መንደር በተፈጸመ ጥቃት ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በጥቃቱ ምክንያት ከሰባ በላይ አባዎራዎች ተፈናቅለው በቴፒ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ መጠለላቸው ተነግሯል። በሸካ አሁንም አካባቢውን ለቃችሁ ሒዱ በሚል ጥቃቱ ተጠናክሮ በመቀጠሉ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆም የአካባቢው ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል። በሸካ ዞን እርምጭ ቀበሌ አካባቢ በሚኖሩ በተወሰኑ ብሄረሰብ አባላት ...
Read More »በአጋሮ ከተማ በተነሳ ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ
በአጋሮ ከተማ በተነሳ ተቃውሞ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዛሬ አርብ የከተማው ከንቲባ አቶ ናዚሙ ሁሴን፣ የጎማ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ራይስ እንዲሁም የድርጅት ቢሮ ሃላፊው አቶ ነዚህ ሙሃመድ አሚን እንዲወርዱ ለመጠየቅ በተሰባሰቡ ነዋሪዎች ላይ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በወሰዱት እርምጃ በሞተስ ሳይክል ሲጓዝ የነበረ አንድ ሰው በጥይት ተመትቶ ህይወቱ አልፏል። በከተማዋ የንግድ ቤቶች ...
Read More »በቡራዩ ነጋዴዎች የንብረት ካሳ አለማግኘታቸውንና ስራም አለመጀመራቸውን ገለጹ
በቡራዩ ነጋዴዎች የንብረት ካሳ አለማግኘታቸውንና ስራም አለመጀመራቸውን ገለጹ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም )ባለሆቴሎቹ ለኢሳት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለደረሰው የንብረት ውድመት የከተማው መስተዳድር የወደመውን ንብረት ምዝገባ እና ግምት ቢያካሂድም እስካሁን ወደስራ እንዲመለሱ ለማድረግ ይህ ነው የሚባል ተግባር አላከናወነም፡፡ የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ በበኩላቸው የወደመውን ንብረት የመመዝገቡ ስራ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡ ለተፈናቃዮቹ ማቋቋሚያም ሆነ ለደረሰው የንብረት ...
Read More »በራያ ህዝብ ላይ የሚደርሱት የመብት ጥሰቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። አሁንም 23 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ናቸው።
በራያ ህዝብ ላይ የሚደርሱት የመብት ጥሰቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። አሁንም 23 ትምህርት ቤቶች እንደተዘጉ ናቸው። ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም )ካለ ሕዝብ ፈቃድ ከወሎ ክፍለሃገር ተወስዶ ወደ ትግራይ እንዲካለሉ የተደረጉት ራያዎች በተደጋጋሚ ጊዜያት የሚያነሱትን የማንነት ጥያቄዎች ለማዳፈን በትግራይ ክልል የሚደርስባቸው መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰቶች ተጠናክረው ቀጥለዋል። በአዲሱ ዓመት የትምህርት ዘመን ህገ መንግስቱ የሰጠን መብት ይከበርልን፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋችን ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 በሃረር ከተማ ስብሰባ እንዳያካሂድ ተከለከለ
አርበኞች ግንቦት7 በሃረር ከተማ ስብሰባ እንዳያካሂድ ተከለከለ ( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም )ክልሉ ለድርጅቱ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓም በጻፈው ደብዳቤ “ በጸጥታ ምክር ቤት ጉዳዩ ታይቶ በክልሉ ባለው ሃገራዊ ሁኔታ አንጻር ተገምግሞ የተጠየቀው ፍቃድ አለመፈቀዱን እንገልጻለን” ብሎአል። ክልከላውን በማስመልከት ልክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ጋቢሳ ተስፋዬና ለጸጥታ ክፍል ሃላፊው አቶ አበበ መብራቱ ስልክ በተደጋጋሚ ብንደውልም ሊመልሱልን አልቻሉም። ...
Read More »