በሸካ ዞን ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 2/2011) በሸካ ዞን ቴፒ በየኪ ወረዳ  እርምጭ ቀበሌ  ጎረፌ በሚባል  መንደር  በተፈጸመ ጥቃት ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ።

በጥቃቱ ምክንያት ከሰባ በላይ አባዎራዎች ተፈናቅለው በቴፒ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ መጠለላቸው ተነግሯል።

በሸካ አሁንም አካባቢውን ለቃችሁ ሒዱ በሚል ጥቃቱ ተጠናክሮ በመቀጠሉ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆም የአካባቢው ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

በሸካ ዞን እርምጭ ቀበሌ  አካባቢ  በሚኖሩ  በተወሰኑ ብሄረሰብ  አባላት ላይ የተካሄደው  ጥቃት  አካባቢውን  ለቃችሁ  ውጡ በሚል  ነው ተብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሸካ ዞን ቴፒ በየኪ ወረዳ  እርምጭ ቀበሌ  ጎረፌ በሚባል  መንደር  በተፈጸመ ጥቃት ስደስት ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጸዋል።

አራት ሰዎች  በስለት  ተቆርጠው  የተገደሉ መሆናቸው ነው የተነገረው።

ጥቃት ደርሶባቸው ቴፒ ሆስፒታል  ገብተው  ከነበሩት መካከልም አንደኛው  ወደ  አማን ሆስፒታል  ለከፍተኛ ህክምና መላኩ ተነግሯል ።

የጥቃቱን ምክንያት በተመከተ አንድ የአካባቢው ነዋሪ አስተያየታቸወን ለኢሳት ገልጸዋል።

በዚሁ ጥቃት ምክንያትም ከሰባ በላይ አባወራዎች በቴፒ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ  ተጠልለው እርዳታ  እየጠየቁ  እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

በሸካ አሁንም አካባቢውን ለቃችሁ ሒዱ በሚል ጥቃቱ ተጠናክሮ በመቀጠሉ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆም የአካባቢው ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።

በሸካ ዞን የጌጪ ወርዳ አስተዳዳሪ አቶ አትርሴ ዳጉሳ ለኢሳት እንደገለጹት ግጭቱ የተከሰተው አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚል ሳይሆን በዞን እንደራጅ ባሉ ሰዎችና ይሕንን በሚቃወሙ መካከል ነው።

ወረዳ አስተዳዳሪው እንዲህ ቢሉም በማሻ እና  ጌጫ ወረዳዎች  እንዲሁም  ኩቢጦና እርምጭ ቀበሌ  ያሉት ነዋሪዎች  የሸካ አመራር  ባደራጃቸው  የጥፋት  ኃይሎች  ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ተብሏል።

እናም ጥቃቱን ለማስቆም  መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ነዋሪዎቹ ጥሪ  አድርገዋል። በከማሻና ጌጫ ወረዳዎችም   ማሳደዱ ቀጥሏል ነው የተባለው።

የመከላከያና የልዩ ሀይል አባላትም ድርጊቱን በዝምታ እየተመለከቱ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።