በቡራዩ ነጋዴዎች የንብረት ካሳ አለማግኘታቸውንና ስራም አለመጀመራቸውን ገለጹ

በቡራዩ ነጋዴዎች የንብረት ካሳ አለማግኘታቸውንና ስራም አለመጀመራቸውን ገለጹ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 02 ቀን 2011 ዓ/ም )ባለሆቴሎቹ ለኢሳት ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለደረሰው የንብረት ውድመት የከተማው መስተዳድር የወደመውን ንብረት ምዝገባ እና ግምት ቢያካሂድም እስካሁን ወደስራ እንዲመለሱ ለማድረግ ይህ ነው የሚባል ተግባር አላከናወነም፡፡
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ በበኩላቸው የወደመውን ንብረት የመመዝገቡ ስራ በቀጣዩ ሳምንት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡
ለተፈናቃዮቹ ማቋቋሚያም ሆነ ለደረሰው የንብረት ውድመት ካሳ ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ለታለመለት አላማ እንዲውል ከሚመለከተው አካል ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል፡፡