(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 29/2011) በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ሳቢያ ከ20 አመት በፊት ተዘግቶ የቆየው የሁመራ አምሃጀር ድንበር የሁለቱ ሃገራት መሪዎች በተገኙበት ዛሬ ተከፈተ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ እንዲሁም የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸውና የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል በተገኙበት የሁለቱ ሃገራት ድንበር ተከፍቷል። የሁለቱ ሃገራት ድንበር በይፋ መከፈቱን የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ሪቫን በመቁረጥ አብስረዋል። የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ...
Read More »በምዕራብ ጉጂ የሰላም ሳምንት ጥሪ ቀረበ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 29/2011)በምዕራብ ጉጂ አባገዳዎች ለሰባት ቀናት የሚቆይ የሰላም ሳምንት ጥሪ አደረጉ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ከሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች በሁለተኛ ደረጃ በምትጠቀሰው የምዕራብ ጉጂ ዞን የተጠራው የሰላም ሳምንት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እንዲሳተፍበት በሚል የተዘጋጀ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በአዶላ ከተማ የሚካሄደው የሰላም ጉባዔ የሰላም ሳምንቱ ዋነኛ ክንውን እንደሆነም ተገልጿል። ፌስቡክን ጨምሮ በማህበራዊ መድረኮች ሳምንቱ ስለሰላም በመስበክ ህዝቡ ስሜቱን እንዲገልጽ በአባገዳዎች በኩል ...
Read More »በጀርመን የሃገሪቱ ፖለቲከኞችና የሃገሪቱ መሪ መረጃ ተሰረቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2011)በጀርመን የኢንተርኔት መረጃ ጠላፊዎች ከመቶ በሚበልጡ የሃገሪቱ ፖለቲከኞችና በሃገሪቱ መሪ ላይ ጭምር የመረጃ ስርቆት መፈጸማቸው ተሰማ። የኢንተርኔት መረጃ ጠላፊዎቹ የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን የግል መረጃ ጭምር ከሰረቁ በኋላ በኢንተርኔት ማሰራጨታቸው ተሰምቷል። ጠላፊዎቹ የጋዜጠኞችንና የኪነጥበብ ሰዎችን መረጃም ሰርቀው ማውጣታቸውም ታውቋል። በጀርመን ዛሬ በደረሰው የዚህ የኢንተርኔት ጥቃት ከመቶ የሚበልጡት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና የኪነጥበብ ሰዎች፣ የግል መረጃዎች፣ የገንዘብ ሚስጥሮች፣ በግል የተጻጻፏቸው ...
Read More »በኦሮሚያ በሌብነት የታሰሩ ከንቲባዎች ቁጥር ሶስት ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2011) በኦሮሚያ ክልል በሌብነት ተጠርጥረው የታሰሩ ከንቲባዎች ቁጥር ሶስት ደረሰ። በአጠቃላይ ከ70 በላይ የስራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ክልል የጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሲሳይ ነጋሽ ትላንት ከሌሎች አራት ሰዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል። ቀደም ሲል የሻሸመኔና የገላን ከተማ ከንቲባዎች የነበሩ ሃላፊዎች መታሰራቸው ይታወሳል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ የነበሩት አቶ ሲሳይ ነጋሽ በቁጥጥር ስር ...
Read More »ሜቴክ ከግማሽ በላይ ሰራተኞቹን ቀነሰ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2011)የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን/ሜቴክ/ካሉት 19 ሺ 5 መቶ ሰራተኞች ከግማሽ በላይ የሚሆኑትን መቀነሱ ተነገረ። መንግስታዊውና ወታደራዊው ተቋም ሜቴክ ሰራተኞቹን ወደ ሌላ መስሪያቤት በማዛወርና በማባረር 8ሺ ብቻ እንዲቀሩት አድርጓል። የሜቴክ የቀድሞ አመራሮች ከፍተኛ የሃገር ሃብት በማባከንና በሌብነት ተጠርጥረው ከተያዙ በኋላ ተቋሙን የማስተካከል ርምጃ ሲወሰድ ቆይቷል። ሜቴክ ሰራተኞችን በማዛወርና በማባረር የቀነሰው አሁን ካለበት ውድቀት ራሱን ለማውጣት መሆኑን የተቋሙ አመራሮች ይናገራሉ። በዚሁም ...
Read More »የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትን ለማስመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2011) በታጣቂዎች ታፍነው የተወሰዱትን የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትን ለማስመለስ ሁሉንም አማራጮች እየተጠቀመ መሆኑን ኦዴፓ አስታወቀ። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ ለኢሳት እንደገለጹት የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳላሳ ቡልቻ በታጣቂዎች ታፍነው ከተወሰዱበት ጊዜ አንስቶ የክልሉ መንግስት ማንኛውንም መንገድ በመጠቀም ለማስመለስ እየተንቀሳቀሰ ነው። በሌላ በኩል በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላን ወረዳ ታፍነው የተወሰዱትን ሶስት ...
Read More »ኦነግ የአካባቢውን ሰላም እያደፈረሰ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2011)የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር የደረሰውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩ የአካባቢው ሰላም እየደፈረሰ መሆኑን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። የኦነግ ለሰላም አለመገዛት ሊሰብሩን የሚፈልጉ ሃይሎች ፍላጎትን ለማሳካት በሚችል መልኩ የኦሮሚያ ክልልን ሰላም አደፍርሷል ብሏል መግለጫው። በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በምእራብ ጉጂ ዞን በየእለቱ የሰው ህይወት እያለፈና ንብረት እየወደመ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገልጿል። የኦሮሚያ ...
Read More »የአሜሪካ ፌደራል መንግስት ተቋማት በከፊል ተዘጉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2011)በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና በኮንግረሱ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት የአሜሪካ ፌደራል መንግስት ተቋማት በከፊል ከተዘጉ 10 ቀናት አለፈ። ችግሩን በንግግር ለመፍታት ትላንት ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር የተደረገውም ውይይት ያለውጤት አብቅቷል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካና በሜክሲኮ ድንበር ላይ ለመገንባት ላቀዱት ግንብ የጠየቁት 5 ቢሊዮን ዶላር በምክር ቤት ተቀባይነት አለማግኘቱ የፈጠረው ውዝግብ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ከስራ ውጭ አድርጎ ሁለተኛውን ሳምንት ...
Read More »በኦሮሚያ 955 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀመሩ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2011)በኦሮሚያ ክልል ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ተዘግተው ከነበሩ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 955ቱ ስራ መጀመራቸው ተገለጸ። የሃገር ሽማግሌዎችና የሚመለከታቸው ወገኖች ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ትምህርት ቤቶቹ መከፈት መቻላቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ በ6 ዞኖች ማለትም በምዕራብ ጉጂ፣በምስራቅ ወለጋ፣ምዕራብ ወለጋ፣በቄለም ወለጋ፣በሆሮጉድሩ ወለጋና በቦረና ዞኖች በአጠቃላይ በጸጥታ ችግር 1ሺ 765 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውም ተመልክቷል። በአሁኑ ወቅት ከሃገር ሽማግሌዎችና ...
Read More »የወረዳ አመራሮችን ለማስለቀቅ አባገዳዎች ሽምግልና መያዛቸው ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 25/2011) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች ያገቷቸውን ሶስት የወረዳ አመራሮችን ለማስለቀቅ አባገዳዎች ሽምግልና መያዛቸው ተገለጸ። ባለፈው ዓርብ ከስብሰባ ሲመለሱ መንገድ ላይ ታፍነው የተወሰዱት የገላና ወረዳ አመራሮች የት እንደሚገኙ የታወቀ ነገር የለም። ታፍነው ከተወሰዱት አንዱ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ እንደሆኑ ታውቋል። በሌላ በኩል ከሞያሌ ሲመለስ በነበረ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ መከፈቱን ተከትሎ በተወሰደ ርምጃ 10 ...
Read More »