(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 20/2011)ኢሕአዴግ ከጥቂት ወራት በኋላ በሚመሰርተው አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ መካተት ለሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሩ ክፍት መሆኑን ግንባሩ አስታወቀ። የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግንባሩ አጋር ድርጅቶችን አካቶ በመዋሀድ አንድ አገር አቀፍ ፓርቲ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚመሠረት መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ‹‹ከጥቂት ወራት በኋላ የአፋር፣ የቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ የሶማሌ፣ ...
Read More »የዮሃንስ አፈወርቅ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)አንጋፋው የዋሽንት ተጫዋች ዮሃንስ አፈወርቅ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ። የዋሽንት ተጫዋቹ ዮሃንስ አፈወርቅ በ72 አመቱ በትናንትናው እለት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ይታወሳል። ወጋየሁ ንጋቱ በተረከው የፍቅር እስከ መቃብር ልቦለድ መጽሀፍ የሚሰማው የዋሽንት ዜማ የዮሃንስ አፈወርቅ ስራ ነው፡፡” የዋሽንት ተጫዋች ዮሃንስ አፈወርቅ ህዝብ ለህዝብ በተሰኘው የኪነ ጥበብ ጉዞ አባል በመሆንም ተሳታፊ እንደነበር ይታወሳል አርቲስት ዮሃንስ አፈወርቅ በአዲስ አበባ ባህልና አዳራሽ ...
Read More »በአቶ በረከትና በአቶ ታደሰ ካሳ ላይ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተፈቀደ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)የአማራ ክልል ፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪ በአቶ በረከት ስምዖንና አቶ ታደሰ ካሳ ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፈቀደ። መርማሪው ትናንት ለችሎቱ ባቀረበው ማብራሪያ ባለፉት 14 ቀናት ያከናወናቸውን የምርመራ ስራዎች አስረድቷል። በዚህም ከዘጠኝ ምስክሮች ቃል መውሰዱን እና በ20 ሰነዶች ላይ ምርመራ መድረጉን መርማሪው ገልጿል። ባለፈው አርብም የዳሸን ቢራ አክሲዮን ማህበር ዳየት ...
Read More »ሁለት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ለህወሃት የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)የራያ ተወላጅ የሆኑ ሁለት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ከህወሃት የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ። የመልቀቂያ ጥያቄውን ያቀረቡት በኩዌት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ አብዱልቃድር ኩቢና በሶማሊያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ ዳሎል አረፈ መሆኗቸው ታወቋል። አቶ አብዱልቃድር ኩቢ የዋጃ ተወላጅ ሲሆኑ አቶ ዳሉል አረፈ ደግሞ የራያ መሆኒ ተወላጅ መሆናቸው ታውቋል። ለህወሃት የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበዋል የተባሉት ሁለት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ናቸው።በኪዌት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት ...
Read More »አንድ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት እየተደረገ ያለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011) አንድ አገራዊ ፓርቲ ለመመስረት እየተደረገ ያለው ጥናት እየተጠናቀቀ ነው መሆኑን ኢህአዴግ አስታወቀ። የዘጠኙንም ክልል ፓርቲዎችን ያካተተ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት የተወሰነው ውሳኔ በ11ኛው የኢሕአዴግ ጉባኤ ላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እየተጓዘ መሆኑን የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በበኩላቸው ከጥቂት ወራት በኋላ የአፋር፣ የቤንሻንጉል ጉምዝ፣ የሶማሌ፣ የኦሮሞ፣ የአማራ . ፓርቲ የሚባል ነገር ...
Read More »በቀይ ሽብር ጊዜ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸመ ኢትዮጵያዊ ጥፋተኛ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 18/2011) በኢትዮጵያ በቀይ ሽብር ጊዜ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸመ ኢትዮጵያዊ በተጭበረበረ መንገድ የአሜሪካ ዜግነት በማግኘቱ በቨርጂኒያ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባለ። መርጊያ ንጉሴ ሃብተየስ የተባለውና የ58 ዓመት ዕድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ የሃገሪቱን ህግ በመጻረር በኢትዮጵያ በቀይ ሽብር ጊዜ መሳተፉን ሳይገልጽ በሃሰት መረጃ የአሜሪካን ዜግነት አግኝቷል። ግልሰቡ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ ጥፋተኝነቱን በማመኑም ለመጭው ግንቦት የመጨረሻውን ፍርድ ሊያገኝ ቀጠሮ መያዙን ጀስቲስ ...
Read More »ብሔራዊ ባንክ ገንዘብ ተመላሽ ያላደረጉ ድርጅቶችን መለየቱ ታወቀ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 17/2011)ለገቢና ለወጭ ንግድ አገልግሎት በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር ወስደውና ምርቶች ወደ ውጪ ልከው ገንዘቡን ወደ ሀገርቤት ያልመለሱ 240 ድርጅቶችን ብሔራዊ ባንክ መለየቱን አስታወቀ። ባለፉት አስራ አራት ዓመታት በርካታ አስመጪዎች የተለያዩ ምርቶችን እንዲያስመጡ ከተለያዩ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶላቸው ነበር። ነገር ግን ምርቱን ሳያስመጡ እንዲሁም ምርት ልከው ተመጣጣኝ የውጭ ምንዛሬን ሀገር ውስጥ ሳያስገቡ በመንግስት በተደረገ ጫና ከብሄራዊ ባንክ እገዳቸው ተነስቶላቸው ተጨማሪ ...
Read More »አዲስ አበባችን ማህበራዊ ንቅናቄ በይፋ ስራ ጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 18/2011)አዲስ አበባችን ማህበራዊ ንቅናቄ በይፋ መመስረቱንና ስራ መጀመሩን አስታወቀ። ንቅናቄው ወደ ስራ ሲገባም የአዲስ አበባ ህዝብ መሰረታዊ ችግሮች ምንድን ናቸው የሚሉትን ሃሳቦች መሰረት በማድረግ ነው ይላሉ የንቅናቄው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ሱራፌል ዘውዱ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አዲስ አበባችን ማህበራዊ ንቅናቄን ለመመስረት አራት ወራትን ፈጅቷል ይላሉ የንቅናቄው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ሱራፌል ዘውዱ። በነዚህ ጊዜያት ውስጥና ከዛም ቀደም ብሎ ...
Read More »የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደር እጦት እየተሰቃየን ነው አሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 18/2011)በአርባ ምንጭ ከተማ ያለው የመልካም አስተዳደር እጦትና ኢሰብአዊ ድርጊት እየተባባሰ መምጣቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጹት እንደ ሃገር መቷል የተባለው ለውጥ አርባ ምንጭ ከተማን አላካተተም። ትላንት ከህወሃት ጋ ሆነው ህዝብን ሲያሰቃዩ የነበሩት አመራሮች አሁንም በስልጣን ላይ መሆናቸው በከተማዋ ያለውን ችግር የከፋ አድርጎታል ይላሉ። በዚህ ጉዳይ ላይ ኢሳት የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም። የህወሃት አገዛዝ ከስልጣን ተወግዶ ...
Read More »በኦዴፓና በአዴፓ ስራአስፈጻሚ አባላት መካካል ውይይት ተካሄደ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት17/2011)በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) እና በአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ስራአስፈጻሚ አባላት መካካል በኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ ባሉ ችግሮች ላይ ውይይት መካሄዱን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። የሁለቱም ፓርቲ ስራ አስፈጻሚዎች ውይይት በጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ከተካሄደ በኋላ ችግሮችን ገምግመው ለውጡን በይበልጥ ለማስቀጠል የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ኦዴፓና አዴፓ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሉ ችግሮች ላይ መክረውም ከተማዋን በጋራ ለመምራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ ...
Read More »