ሁለት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ለህወሃት የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)የራያ ተወላጅ የሆኑ ሁለት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ከህወሃት የመልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ።

የመልቀቂያ ጥያቄውን ያቀረቡት በኩዌት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ አብዱልቃድር ኩቢና በሶማሊያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ ዳሎል አረፈ መሆኗቸው ታወቋል።

አቶ አብዱልቃድር ኩቢ የዋጃ ተወላጅ ሲሆኑ አቶ ዳሉል አረፈ ደግሞ የራያ መሆኒ ተወላጅ መሆናቸው ታውቋል።

ለህወሃት የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበዋል የተባሉት ሁለት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ናቸው።በኪዌት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ አብዱልቃድር ኩቢና በሶማሊያ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ዲፕሎማት የሆኑት አቶ ዳሉል አረፈ ናቸው።

ሁለቱ ዲፕሎማቶች የመልቀቂያ ጥያቄውን ያቀረቡበት ዋነኛ ምክንያትም የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ በህወሃት እየደረሰበት ያለውን ግፍና በደል  በዝምታ ማየት ባለመቻላቸው መሆኑ ታውቋል።

ዲፕሎማቶቹ የራያ ህዝብ ማንነቱ እንዲከበርለት፣መገለጫው በሆነው በወሎ አስተዳደር በአማራ ክልል ስር ልካለል በሎ በሰላማዊ መንገድ መጠየቁ ለእንግልት፣ለመፈናቀል፣ለእስራት ተዳርገዋል።

በርካታ የራያ ወጣቶችም ህይወታቸውን አተዋል።

የመልቀቂያ ጥያቄውን ያቀረቡት ሁለቱም ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የራያ ተወላጆች መሆናቸው ታውቋል።

አቶ አብዱል ቃድር ኩቢ የራያ ዋጃ ተወላጅ ሲሆኑ አቶ ዳሉል አረፈ ደግሞ ውልደታቸው በራያ መሆኒ እንደሆነ ነው የታወቀው።

ዲፕሎማቶቹ በህወሃት ውስጥ የራያ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ ከሌላው ተለይተው መበደላቸው፣ በጥርጣሬና በጥላቻ ስሜት መታየታቸው ከህወሃት ጋር መቀጠል እንዳላስቻላቸው ነው በመልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩት።

ህወሓት እንደ ሃገር የታየውን የለውጥ ጭላንጭል ለማጨለም የሚጓዝበት የተንኮል አካሄድ ከድርጅቱ ጋር እንዲቀጥሉ እንዳላደረጋቸውም በመልቀቂያቸው ላይ አስፍረዋል።

የሁለቱ ዲፕሎማቶች አቋምም የራያ ህዝብ የሚያነሳቸው ሁሉም ጥያቄዎች ካልተመለሱ፣በራያ ህዝብ ላይ እስር፣እንግልትና ግድያ የፈጸሙ አካላት ለህግ መቅረብ አለባቸው።

ይህ ካልሆነ ግን ከድርጅቱ መልቀቅ ብቻ ሳይሆን ህወሃትን እስከመጨረሻው እንታገለዋለን ሲሉ በመልቀቂያቸው ላይ ማቅረባቸውም ታውቋል።