የዮሃንስ አፈወርቅ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 19/2011)አንጋፋው የዋሽንት ተጫዋች ዮሃንስ አፈወርቅ የቀብር ስነስርአት ተፈጸመ።

የዋሽንት ተጫዋቹ ዮሃንስ አፈወርቅ በ72 አመቱ በትናንትናው እለት ከዚህ አለም በሞት መለየቱ ይታወሳል።

ወጋየሁ ንጋቱ በተረከው የፍቅር እስከ መቃብር ልቦለድ መጽሀፍ የሚሰማው የዋሽንት ዜማ  የዮሃንስ አፈወርቅ ስራ ነው፡፡”

የዋሽንት ተጫዋች ዮሃንስ አፈወርቅ ህዝብ ለህዝብ በተሰኘው የኪነ ጥበብ ጉዞ አባል በመሆንም ተሳታፊ እንደነበር ይታወሳል

አርቲስት ዮሃንስ አፈወርቅ በአዲስ አበባ ባህልና አዳራሽ ለረጅም ጊዜ ማገልገሉን ዘገባዎች አመልክተዋል።

አርቲስት ዮሃንስ በጎጃም ወስጥ በቀድሞው የአገው ምድር አውራጃ ባንጃ ወረዳ ታህሳስ 3 / 1939 መወለዱን  የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል።

ስርዓተ ቀብሩም ዛሬ ከቅኑ 9 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

አርቲስት ዮሃንስ አፈወርቅ ባለትዳርና የ4 ወንዶቹና የ1 ሴት ልጅ አባት ነበር።