(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) በሃዋሳ ከተማ በተነሳው ግጭት ለ10 ሰላማዊ ሰዎች ሞትና ለ80 ሰዎች መቁሰል ተጠያቂ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከ200 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። በግጭቱ 3ሺ 500 ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ሆስፒታል አልጋ ላይ የነበሩ ሰዎች ጭምር በጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውም ታውቋል። የሲዳማ ዞን አስተዳደር አቶ አክሊሉ አዱላ አዲስ አበባ ለሚታተመው ሪፖርተር የእንግሊዝኛ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ በግጭቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሳታፊ ...
Read More »አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 18/2010) አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከደኢሕዴን ሊቀመንበርነታቸው በፈቃዳቸው ለቀቁ። የደኢሕዴን ሊቀመንበር ከሆኑ ሶስት ወር ያልሞላቸው አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የለቀቁበት ምክንያት ግን አልታወቀም። በቅርቡ በሃዋሳ በተፈጠረው ግጭት የሲዳማ ዞን እና የወረዳ አመራሮች በፈቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል። ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 226 ሰዎች መታሰራችውም ታውቋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት ከዶክተር አብይ አህመድ ጋር መወዳደራቸውም ይታወሳል ...
Read More »የጣሊያን መንግስት ስደተኞችን የጫኑ ሁለት መርከቦችን አገደ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) የጣሊያን መንግስት ስደተኞችን የጫኑ ሁለት መርከቦችን በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ አግኝቻቸዋለሁ በሚል ማገዱን አስታወቀ። የጣሊያን መንግስት አግቻቸዋለሁ ያላቸው መርከቦች 226 ከአዳጋ የተረፉ ስደተኞችን ጭነው እንደነበርም ታውቋል። ከሊቢያ ወደብ የተነሱትንና አደጋ ላይ ወድቀው የነበሩትን ስደተኞች የጫኑት መርከቦች የሆላንድን ባንዲራ ሲያውለበልቡ እንደነበርም መረጃው አመልክቷል። በጣሊያን በቅርብ አዲስ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር መመረጣቸውን ተከትሎ የሜዲትራኒያንን በባህር አቋርጠው የሚመጡ ስደተኞችን ሃገሪቱ አልቀበልም ...
Read More »ኢሳትና ኦ ኤም ኤንን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በነጻነት እንዲታዩ ተፈቀደ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) ኢሳትና ኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥንን ጨምሮ በኢትዮጵያ ታግደው የነበሩ 264 ድረገጾች በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻነት እንዲታዩ መፈቀዱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት የሌሎች ነጻነቶች መሰረት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል። መንግስት በዚህ መነሻነትም የታገዱት ቴሌቪዥኖችና ድረገጾች እንዲከፈቱ ማድረጉን አመልክተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ጨምረው እንደገለጹት ነጻ የሃሳብ ዝውውር አሳታፊና ሃላፊነት የሚሰማውን ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠቡን አስታወቀ
አርበኞች ግንቦት7 አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠቡን አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከሰኔ 15 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አርበኞች ግንቦት 7 “በማናቸውም መልኩ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ምንም አይነት አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ ታቅቧል” ብሎአል። “ኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛዉም አካባቢ የሚገኙ የነጻነት ታጋዮቻችን ከማናቸውም የአመጽ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ድርጅታዊ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል” ያለው ድርጅቱ ውሳኔው “በኢህአደግ ውስጥ ያሉ ...
Read More »በቄለም ወለጋ ዞን የሚታዬው ውጥረት አለመቀነሱን የአማራ ተወላጆች ተናገሩ
በቄለም ወለጋ ዞን የሚታዬው ውጥረት አለመቀነሱን የአማራ ተወላጆች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በ1977 ዓም በነበረው ድርቅ ከወሎ ክፍለ ሃገር ተሰደው በቄለም ወለጋ መቻራ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶአደሮች ለኢሳት እንደተናገሩት ትናንት ከጠዋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚሉ ወጣቶችና በእነሱ መካከል በነበረው ግጭት 11 ሰዎች ቆስለዋል። ግጭቱን ለማብረድ አባገዳዎች ጣልቃ ገብተው ለማስቆም ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ...
Read More »የኤርፖርቶች ድርጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሸጥ አሳስቦኛል አለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች በሽርክና ይተላለፋል መባሉ እንዳሳሰባቸው የኤርፖርቶች ድርጅት የቀድሞ ሰራተኞች ገለጹ። ሰራተኞቹ ስጋታቸውን የገለጹት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በ2009 በጸደቀው አዋጅ መሰረት በመቀላቀሉ ነው። በየትኛውም ዓለም የኤርፖርቶች ድርጅት ከመንግስት ቁጥጥር ስር አይወጣም ሲሉም ያክላሉ። የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ታላላቅ የመንግስት ተቋማትን በሽርክና ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች ለማዘዋወር ውሳኔ ማሳልፉ ...
Read More »ህወሃት የሰማዕታት ቀን በሚል የሚከበረውን በአል የተቃውሞ መገለጫ አድርጎት ዋለ
ህወሃት የሰማዕታት ቀን በሚል የሚከበረውን በአል የተቃውሞ መገለጫ አድርጎት ዋለ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ የትግራይ ሰማዕታት ቀን በሐውዜን ከተማ በተከበረበት እለት የተያዙት መፈክሮች ህወሃት በቅርቡ የኢትዮ- ኤርትራን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተቸት ያወጣውን መግለጫ የሚያንጸባርቁ ናቸው። የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ያልተሳተፉበት ሰላም ዘላዊ ሰላም አይሆንም፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች ለዘላቂ ሰላም ጣምራ ክንድ ...
Read More »በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአርባምንጭ ወጣቶች እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአርባምንጭ ወጣቶች እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የሽብር ወንጀል ሰበብ ተከሰው በእስር ቤት ከቆዩ በሁዋላ በቅርቡ የተለቀቁ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ ወደ አካባቢያቸው ቢመለሱም፣ ፖሊሶች እያሳደዱዋቸው ነው። ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈታው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ትናንት በፖሊሶች ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበታል። ከጌታሁን በየነ ጋር አብሮ የነበረው ጓደኛው ወጣት ካሳሁን፣ ...
Read More »ሪክ ማቻር ወደ ገለልተኛ አገር ሊዛወሩ ነው
ሪክ ማቻር ወደ ገለልተኛ አገር ሊዛወሩ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ሱዳን ላለፉት 4 አመታት የቆየውን ግጭት ለማስቆም የተቃዋሚ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር አሁን ከሚገኙበት ደቡብ አፍሪካ ወጥተው ወደ ገለልተኛ አገር ሊሄዱ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። እቅዱ በኢጋድ አገራት ተቀባይነት አግኝቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ውጤት አልባ ሆኗል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ከቀድሞው ምክትል ...
Read More »