ሪክ ማቻር ወደ ገለልተኛ አገር ሊዛወሩ ነው

ሪክ ማቻር ወደ ገለልተኛ አገር ሊዛወሩ ነው
(ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ሱዳን ላለፉት 4 አመታት የቆየውን ግጭት ለማስቆም የተቃዋሚ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር አሁን ከሚገኙበት ደቡብ አፍሪካ ወጥተው ወደ ገለልተኛ አገር ሊሄዱ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። እቅዱ በኢጋድ አገራት ተቀባይነት አግኝቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ውጤት አልባ ሆኗል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ከቀድሞው ምክትል ፕሬዚዳንት ሪክ ማቻር ጋር አብረው ለመስራት ፍላጎት የሌላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
የሚቀጥለው ድርድር ሱዳንና ኬንያ ውስጥ የሚካሄድ ሲሆን፣ ሁለቱ ሃይሎች የሰላም ስምምነት ላይ ካልደረሱ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው አደራዳሪዎች አስጠንቅቀዋል።