በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአርባምንጭ ወጣቶች እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአርባምንጭ ወጣቶች እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው
(ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የሽብር ወንጀል ሰበብ ተከሰው በእስር ቤት ከቆዩ በሁዋላ በቅርቡ የተለቀቁ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ ወደ አካባቢያቸው ቢመለሱም፣ ፖሊሶች እያሳደዱዋቸው ነው። ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈታው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ትናንት በፖሊሶች ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበታል። ከጌታሁን በየነ ጋር አብሮ የነበረው ጓደኛው ወጣት ካሳሁን፣ በከተማው የጸጥታ ክፍል ሃላፊ ገበየሁ አባጫላ ተተኩሶበት ተርፏል።
ከእስር የተፈቱት ወጣቶች ደህንነቶችና የከተማው ፖሊሶች እያሳደዱዋቸው እንደሆነ በምሬት ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የለውጥ እንቅስቃሴ ለማደናቀፍ ያሰቡ የደኢህዴን ካድሬዎች የሚፈጸሙት ተግባር በፍትነት እንዲቆምላቸው ተማጽነዋል።