ኢሳትና ኦ ኤም ኤንን ጨምሮ ሌሎች መገናኛ ብዙሃን በነጻነት እንዲታዩ ተፈቀደ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 15/2010) ኢሳትና ኦ ኤም ኤን ቴሌቪዥንን ጨምሮ በኢትዮጵያ ታግደው የነበሩ 264 ድረገጾች በኢትዮጵያ ውስጥ በነጻነት እንዲታዩ መፈቀዱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡

ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት የሌሎች ነጻነቶች መሰረት መሆኑን የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ ገልጸዋል።

መንግስት በዚህ መነሻነትም የታገዱት ቴሌቪዥኖችና ድረገጾች እንዲከፈቱ ማድረጉን አመልክተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ጨምረው እንደገለጹት ነጻ የሃሳብ ዝውውር አሳታፊና ሃላፊነት የሚሰማውን ዜጋ ለመፍጠር አስፈላጊ ነው።

የነጻ ገበያ መርህም ወደ እውነት ያደርሰናል ብለዋል።