በአርባምንጭ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ተካሄደ

በአርባምንጭ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ተካሄደ (ኢሳት ዜና ግንቦት 17 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከንጋቱ 11 ሰዓት ላይ የአርሶአደሮችን ቤት ለማፍረስ በአጋዚ፣ በልዩ ሃይል እና በአካባቢው ፖሊሶች ታጅቦ የተገኘው አፍራሽ ግብረሃይል ተቃውሞ አጋጥሞታል። አርሶአደሮች ከቀያችን የምታፈናቅሉን እኛን ገድላችሁ ነው የሚል አቋም በመያዛቸው ፣ ወታደሮች በህዝቡ ላይ የጭስ ቦንብ በመወርወርና ተኩስ በመክፈት ለመበተን ሞክረዋል። ህዝቡ ሲሸሽ እንደገና ...

Read More »

አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ልታደርገው የነበረውን ውይይት ሰረዘች

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010) አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ልታደርገው የነበረውን ውይይት መሰረዟን አስታወቀች። ስለስብሰባው አስብበታለሁ ስትል የከረመችው ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ በማንኛውም ሰአት ከአሜሪካ ጋር ውይይት ለማድረግ ፍላጎት አለኝ ስትል አስታውቃለች። ደቡብ ኮሪያ አሜሪካ ታሪካዊ የተባለውን ይህንን ውይይት በመሰረዟ አዝኛለሁ ማለቷ ታውቋል። ከቀናት በፊት ነበር ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካ ጋር የታሰበውን ውይይት በአሜሪካ በኩል የአስገዳጅነት ስሜት ታይቷል በሚል ውይይቱን ልሰርዝ እችላለሁ ስትል ያስጠነቀቀችው። ...

Read More »

ሁለት አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010) ሁለት አንጋፋ ሙዚቀኞች ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ። አንጋፋዋ የትግርኛ ሙዚቃ ተጫዋች እና ክራር ደርዳሪ ጸሃይቱ ባራኪ በ 79 ዓመቷ ህይወቷ አልፏል። የክቡር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍል ባልደረባ፣የሙዚቃ አቀናባሪ እና ደራሲ ሻለቃ ግርማ ሃድጎም በ90 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። በኢትዮጵያ ኪነጥበብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበራቸው ሁለቱ ኤርትራውያን ህይወታቸው ያለፈው በዚህ በያዝነው ሳምንት ነው። በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1931 ኤርትራ ...

Read More »

የነ አቶ መላኩ ፈንታ ክስ ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010)አቶ መላኩ ፈንታና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስን ጨምሮ በሌብነት ወንጀል የተከሰሱ ታዋቂ ባለሀብቶች ክሳቸው መቋረጡን ፋና ዘገበ። የእነ እቶ መላኩ ክስ መቋረጥ የሕወሃት ንብረት በሆነው  ፋና በሮድካስቲንግ በይፋ ከተዘገበ በኋላ ዜናው ከድረገጹ እንዲነሳ መደረጉ ታውቋል።ከአንድ ሰዓት በኋላ ደግሞ ክሳቸው እንዲቋረጥ አቃቤ ህግ ጠየቀ ሲል ሌላ ዘገባ አቅርቧል። በሌብነት ወንጀል ተከሰው የነበሩት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ...

Read More »

ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሜቴክ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17 /2010) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን የሜቴክ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ። በቅርቡ የኢንደስትሪ ሚኒስተር ሆነው የተሾሙት ዶክተር አምባቸው መኮንን አቶ ደመቀ መኮንንን ተክተው የቦርድ ሊቀመንበር ሆነዋል። የሕወሃቱ አቶ አስመላሸ ወልደ ስላሴም የሜቴክ ቦርድ አባል ሆነዋል። ከፖለቲካ መድረኩ የተገለሉ ሰዎች ተመልሰው ወደ ሃላፊነት መምጣታቸው አነጋጋሪ ሆኗል። በመንግስት 10 ቢሊዮን ብር በጀት የተቋቋመው የመሰረታዊ ብረታብረት ...

Read More »

ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010) ከኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን ደጋ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ900 በላይ የአማራ ተወላጆች ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸው ተገለጸ። ተፈናቃዮቹ በአማራና ኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ትብብር በወልዲያና በጭፍራ መካከል በሚገኝ ሃሮ ተብሎ በሚጠራ በረሃ ላይ ሰፍረው የሚገኙ ሲሆን ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱም በመከላከያ ሰራዊት እየተጠበቁ መሆናቸውም ተገልጿል። አካባቢው ደረቅ መሆኑና ውሃ ማግኘት አለመቻሉ ህጻናት ለበሽታ እየተጋለጡ መሆናቸውን ከስፈራው ያገኘነው መረጃ ...

Read More »

በአርባምንጭ ከተማ በፌደራል ፖሊስና በነዋሪው መካከል ግጭት ተፈጠረ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 17/2010)በአርባምንጭ ከተማ በፌደራል ፖሊስና በነዋሪው መካከል ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ። ጉርባ በተሰኘው የከተማው ክፍል መኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ የተሰማራውን ግብረሃይል ነዋሪው ማስቆሙን ተከትሎ በመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ወደ ጉርባ የገባው የፌደራል ፖሊስ ህዝቡ ላይ መተኮሱን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከ20 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውም ታውቋል። ከ4ሺህ በላይ ነዋሪ በላዩ ላይ ቤት መፍረሱ ሌላውን የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪን እንዳስቆጣም ለማወቅ ተችሏል። ሻራ በተሰኘውም መንደር በተመሳሳይ ...

Read More »

በሶማሊ ክልል አብዲ ኢሌን በመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል

በሶማሊ ክልል አብዲ ኢሌን በመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች ቀጥለዋል (ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በሊበን ዞን በዶሎ አዶ ትናንት የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፣ አብዲ ኢሌ ሚሊሺያዎቹን በማዘዝ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጉን የአካባቢው ተወላጆች ገልጸዋል። ተቃውሞውን ለመበተን ልዩ ሃይሎች በወሰዱት እርምጃ እስካሁን ድረስ 3 ሰዎች መገደላቸውንና ከ10 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ተወላጆቹ ተናግረዋል። ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ...

Read More »

መከላከያው ከእነ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ እጅ እየወጣ ነው ተባለ

መከላከያው ከእነ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ እጅ እየወጣ ነው ተባለ (ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) ወታደራዊ ምንጮች እንደሚገልጹት-አብዛኞቹ ከጄኔራልነት በታች ማዕረግ ያላቸው መኮንኖችና ወታደሮች ፣ጄ/ል ሳሞራ የኑስ የሚመራውን በ8 ጄኔራሎች የተዋቀረውን ወታደራዊ እዝ ለመቀበል ፍላጎት እያጡ ነው። የበታች መኮንኖችና ወታደሮች ለውጥ እየፈለጉ መምጣታቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በዚህም ሳቢያ ቁንጮ ሹመኞቹ ትዕዛዞችን እንደ ወትሮው ማስፈጸም እየተቸገሩ ነው ይላሉ። ለውጡ ወታደራዊ ተቋማቱንም ...

Read More »

በአፋርና አማራ ክልል ድንበር ላይ በተፈጠረው ግጭት የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው

በአፋርና አማራ ክልል ድንበር ላይ በተፈጠረው ግጭት የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ/ም) በአፋርና በአማራ ክልል አቅራቢያ በደቡብ ወሎ አካባቢ ሰሞኑን የተቀሰቀሰው ግጭት የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። ሁለቱ ክልሎች ችግሮቻቸውን በውይይት እንደፈቱ በመገናኛ ብዙሃን ተናግረው የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱ እንደገና አገርሽቶ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል። በግጭቱ ዙሪያ የሁለቱ ክልል ባለስልጣናት እስካሁን ...

Read More »