ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት በስድስት ጋዜጠኞች ላይ የመረሰተውን የሽብርተኝነት ክስ በፍጥነት እንዲያነሳ፤ መቀመጫውን ኒው ዮርክ ያደረገው ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት-ሲ.ፒ.ጄ ጠየቀ። ሲ.ፒ.ጄ ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ መንግስት አዲስ ባወጣው የፀረ-ሽብር ህግ መሰረት ሰሞኑን ስድስት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በ 24 ሰዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መመስረቱን በመጥቀስ፤ ክስ ከተመሰረተባቸው ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ በእስር ...
Read More »አቤ ቶክቻው ተሰደደ
ህዳር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለዛ ባለው አዝኛኝ ጽሁፉ ፖለቲካውን እያዋዛ የህብረተሰቡን ብሶት ሲያሰማ የቆየው “አቤ ቶክቻው” አገር ለቅቆ ወጣ። አቤ ቶክቻው ቀደም ሲል ባውራምባ ታይምስ፤አሁን ደግሞ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን እያዋዛ በማቅረቡ በተደጋጋሚ ከደህንነት ሀይሎች ማስጠንቀቂያ ሲደርሰው ቆይቷል። በተለይ ባለፈው ሳምንት፦” ጠቅላይ ሚኒስትሬ እንደሚያነቡኝ ባወቅኩ ጊዜ ደስ አለኝ”በሚል ርዕስ አቶ መለስ የዘንድሮውን ፓርላማ የ ስራ ዘመን ሲከፍቱ ...
Read More »በዋካ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የቶጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የህዝቡ ጥያቄ ፍትሀዊ ሆኖ እያለ እኛ ግን እስከዛሬ ስናፍነው ነበር በማለት ስልጣናቸውን ለቀቁ
ህዳር 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዋካ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የቶጫ ወረዳ አስተዳዳሪ የህዝቡ ጥያቄ ፍትሀዊ ሆኖ እያለ እኛ ግን እስከዛሬ ስናፍነው ቆይተናል፣ ከእናንተ ጋር ከእንግዲህ አልሰራም በማለት ስልጣናቸውን ለቀቁ የኢሳት የደቡብ ወኪል እንደገለጠው አስተዳዳሪው አቶ ፈቃዱ ወልደ ሩፋኤል “የህዝቡ ጥያቄ ፍትሃዊ ሆኖ እያለ፣ እኛ ግን ጥያቄውን ለማፈን በተደጋጋሚ ሙከራ አድርገናል” በማለት ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል። እርሳቸውን ተከትለው ሌለው ስልጣን ...
Read More »በእስር ላይ በሚገኙት ፖለቲከኞች ላይ አሰቃቂ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ታወቀ
ህዳር 1 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን እንደገለፀው ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ.ም ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይቀርባሉ ተብሎ ጊዜ ቀጠሮ የተሰጣቸው የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዷለም አራጌ፣ የፓርቲው የአመራር አባላት ናትናኤል መኮንን፣ አሳምነው ብርሃኑ፣ የመኢዴፓ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ዘመኑ ሞላ እና ...
Read More »የኢህአዴግ መንግሥት ሽብርተኞች ብሎ በአንደኛ ተከሳሽ ኤልያስ ክፍሌ የክስ ፋይል በከሰሳቸው ላይ ዐቃቤ- ሕግ የሰው ምሥክሮችን አሰማ
ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት ሽብርተኞች ብሎ በአንደኛ ተከሳሽ ኤልያስ ክፍሌ የክስ ፋይል የከሰሳቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢብዴፓ) ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚያብሄር፣ የአውራምባ ታይምስ ምክትል ዋና አዘጋጅ ውብሸት ታዬ፣ ሂሩት ክፍሌ እና የፍትህ ጋዜጣ ዓምደኛ ርእዮት ዓለሙ ላይ ዐቃቤ- ሕግ የሰው ምሥክሮችን አሰማ፤ የድምጽና የምስል ማስረጃዎችን ደግሞ ለማቅረብ ለዓርብ ህዳር 1 ቀን 2004 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ...
Read More »የስምንተኛ ክፍል የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት መጽሀፍ አንዳንድ ገጾች ተቀደው እንዲያቃጥሉ ታዘዙ
ጥቅምት 30 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብዙ ሚሊዮኖች ዶላር ወጥቶበት እንዲታተም በተደረገው የስምንተኛ ክፍል የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት መጽሀፍ ውስጥ “ተማሪዎችን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርጉ የሚያበረታቱ ጽሁፎች ተካትተዋል” በሚል ምክንያት፣ ተማሪዎችና መምህራን የመጽሀፉን አንዳንድ ገጾችን ቀደው እንዲያቃጥሉ ታዘዙ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው መጽሀፉ እጅግ ውድ በሆነ ዋጋ ታትሞ ወደ አገር ውስጥ የገባ ነው። መጽሀፉ ባለፈው መስከረም ወር በሚታደልበት ጊዜ ተማሪዎች መጽሀፉን ቀድደው ...
Read More »“ከኢትዮጵያ ጋር የረዥም ጊዜ ግንኙነት ቢኖረንም ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ግን ዝም እንድንል የሚያደርገን አይደለም” ሲሉ የጀርመን ምክር ቤት አባላት አስታወቁ
ጥቅምት 29 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ከኢትዮጵያ ጋር የቆየና የሰነበተ የረዥም ጊዜ ግንኙነት አለን፤ይህ ግን በኢትዮጵያ እየታየ ስላለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዝም እንድንል የሚያደርገን አይደለም” ሲሉ የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት አስታወቁ። የምክር ቤት አባላቱ ይህን ያስታወቁት በቅርቡ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት አስመልክቶ ከትናንት በስቲያ በሰጡት ወቅት ነው። የሊበራል ፓርቲ ተወካዩዋ ወይዘሮ ማርቲና ሹስተር ኢትዮጵያ አዲስ ባወጣችው የፀረ-ሽብር ህግ ...
Read More »እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊው የሆነ ዜጋዋን አምባሳደር አድርጋ ሾመች
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ በ14 አመት እድሜው እኤእ በ1972 ወደ እስራኤል የተጓዘው ራቻሚም ኢላዛር በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል። ራቻሚም ቴላቪቭ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በዲግሪ የተመረቀ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ ላለፉት 30 አመታትም በጋዜጠኝነት ማገልገሉ ታውቋል።
Read More »በአዲስ አበባ ከፍተኛ የውሀ እጥረት ተከሰተ
ዘገቢያችን እንደገለጠው በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፈው አንድ ሳምንት ጀምሮ ውሀ የሚባል ነገር የለም። በገርጂ፣ አቃቂ ፣ አዲሱ ገበያ፣ መገናኛና በሌሎችም አካባቢዎች ነዋሪዎች ለመጠጥ የሚሆን ውሀ አጥተው ተቸግረዋል። የአዲስ አበባ መስተዳዳር የውሀ ባለስልጣናት ችግሮች መከሰታቸውን አምነው፣ ችግሮቹ የተፈጠሩት አንዳንድ የማስተላለፊያ መስመሮች በመበላሸታቸውና ክረምቱ ማለቁን ተከትሎ የውሀ እጥረት በማጋጠሙ ነው። እንደ ባለስልጣኖቹ ገለጣ ችግሮቹ በአብዛኛው በሚቀጥሉት 2 ወራት ውስጥ ይፈታሉ። 25 ...
Read More »የህወሐት ነባር አመራሮች በሰበብ አስባባቡ ስራ እየለቀቁ አንዳንዶችም በቅጣት በማይመጥናቸው ቦታ እየተመደቡ መሆኑ ታወቀ
ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የኢፈርት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አባዲ ዘሙ ከሀላፊነታቸው ተነስተው በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ሐይሌ ኪሮስ ገሰሰ የስራ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ሀላፊነታቸውን እንዲለቁ ተደርገዋል። አቶ ሀይለ ኪሮስ ገሰሰ ከቻይና አምባሳደርነት ሲነሱ የቀድሞውን የዶ/ር ተቀዳ አለሙን የምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትርነት ቦታ እይዛለሁ ብለው ገምተው የነበረ ቢሆንም፣ ቦታው ለአቶ ብርሀነ ...
Read More »